ጥያቄ፤
ጋብቻን የመጨረሻ ማድረግ - ቁልፉ ምንድነው?
መልስ፤
ሐዋርያው ጳውሎስ ይላል፣ ሚስት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ “የታሰረች” መሆንዋን (ሮሜ 7፡2)። እዚህ ያለው መርሕ፣ ባል ወይም ሚስት መሞት ይኖርባቸዋል፣ የጋብቻ እስር ከመፍረሱ በፊት። ይህ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነው፣ ነገር ግን በዘመናዊው ኅብረተሰባችን ጋብቻ የሚያበቃው በፍቺ ነው፣ 51 ከመቶ የሚሆነው። ያ ማለት፣ “ሞት እስኪለየን ድረስ” ብለው ከማሉት ጥንዶች ግማሹ ያንን መሐላ አፍርሰዋል።
ተጋቢ ጥንዶች ምን ማድረግ ይችላሉ፣ ጋብቻቸው ዘላቂ መሆኑን ለማረጋገጥ? የመጀመሪያውና እጅግ ጠቃሚው ጉዳይ ለእግዚአብሔርና ለቃሉ መታዘዝ ነው። ይህ መርሕ ነው ከጋብቻ በፊት ገዢ መሆን ያለበት። እግዚአብሔር ብሏል፣ “ ሁለቱ ሳይስማሙ መንገድ ሊሄዱ ይችላሉን?” (አሞጽ 3፡3)። አዲስ ለተወለደ አማኝ፣ ይህ ማለት የቀረበ ወዳጅነትን አማኝ ካልሆነ ከማንም ጋር ማድረግ እንደሌለበት ነው። “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?” (2 ቆሮንቶስ 6፡14)። ይህን አንድ መርሕ ብንከተል ኋላ ላይ በትዳር ከሚመጣው በርካታ የልብ ቁስለትና መከራ ሊያድን ይችላል።
ሌለኛው መርሕ፣ እሱም የትዳርን ዘላቂነት የሚጠብቅ፣ ባል እግዚአብሔርን ታዝዞ ሚስቱን እንደ ገዛ ሥጋው መውደድ፣ ማክበር፣ እና መጠበቅ እንደሚኖርበት ነው (ኤፌሶን 5፡25-31)። ተጓዳኙ መርሕ ሚስት መጠበቅ የሚኖርባት እግዚአብሔርን መታዘዝና ለባሏ መታዘዝ እንደሚኖርባት ነው “ለጌታ እንደሚደረግ” (ኤፌሶን 5፡22)። በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ ጋብቻ በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ለሚኖረው ግንኙነት ማሳያ ነው። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ራሱን ሰጥቷል፣ ይወዳታልም፣ ያከብራታልም፣ እንደ “ሙሽራው” ይጠብቃታልም (ራዕይ 19፡7-9)።
እግዚአብሔር ሔዋንን ወደ አዳም ሲያመጣት በመጀመሪያው ጋብቻ፣ እሷ የተሠራችው ከእሱ “ሥጋና አጥንት” ነው (ዘፍጥረት 2፡21) እነርሱም “አንድ ሥጋ” ሆኑ (ዘፍጥረት 2፡23-24)። አንድ ሥጋ መሆን ማለት ከሥጋዊ ኅብረት በላይ ነው። እሱ ማለት የሐሳብና የነፍስ ግንኙነት ነው፣ ከአንድ ምድብ። ይህ ግንኙነት ከአካላዊ ወይም ስሜታዊ ማራኪነት አልፎ የሚሄድ ነው፣ ወደ መንፈሳዊው ዓለም “አንድነት”፣ ያም ሊገኝ የሚችለው ሁለቱም ተጓዳኞች ለእግዚአብሔርና ለእርስ በርሳቸው ሲገዙ ብቻ ነው። ይህ ግንኙነት “እኔ እና የኔ” የሚለውን ማዕከል አያደርግም፣ “እኛ እና የእኛ” እንጂ። ይህም አንደኛው የዘላቂ ጋብቻ ምሥጢር ነው። ጋብቻን እስከ ሞት ድረስ ዘላቂ ማድረግ ሁለቱም ተጓዳኞች ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ነው። አንዱ ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ላይ ያለውን ግንኙነት ተጨባጭ ሲያደርግ፣ በባልና ሚስት መካከል የሚኖረውን ጎናዊ ግንኙነት ዘላቂ ወደሚያደርግ ዋስትና ያመራዋል፣ እና ስለዚህ እግዚአብሔርን የሚያከብር።
English
ጋብቻን የመጨረሻ ማድረግ - ቁልፉ ምንድነው?