settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ሴጋ መምታት፤በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ኃጥአት ነውን?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ በግልጽ ሴጋ መምታትን አይጠቅስም ወይም ሴጋ መምታት ኃጥአት ይሁን ወይም አይሁን አይጠቅስም፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት 38፤9-10 ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ሴጋ መምታትን በተመለከተ በጣም በተደጋጋሚ የአውናን ታሪክ እንደሆነ አመልክቷል፡፡ ጥቂቶች ይህንን ምንባብ በመሬት ላይ “ዘርህን ማፍሰስ” ኃጥአት ነው እያለ እንዳለ ይተረጉማሉ፡፡ ሆኖም ግን ያ በትክክለኛው ምንባቡ እያለ ያለው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር አውናንን የወቀሰው “ዘሩን በማፍሰሱ” አይደለም ነገር ግን አውናን ለእርሱ ወንድም ውርሱን የመስጠት ግደታውን ለማሟላት እምቢተኛ በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡ ምንባቡ ስለ ሴጋ መምታት አይደለም ነገር ግን ይልቅ የቤተሰብን ግደታ ስለ ማሟላት ነው፡፡ ሴጋ መምታት ኃጥአት ስለመሆኑ አንዳንድ ጊዜ እንደ ማረጋገጫ ጥቅም ላይ የዋለው ምንባብ የማቴዎስ ወንጌል 5፤27-30 ነው፡፡ ኢየሱስ የአመንዝራነትን አስተሳሰብ ተቃውሞ ተናግሯል እናም ከዚያ “ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት” ይላል፡፡ በተመሳሳይ በዚህ ምንባብ እና በሴጋ መምታት መሐከል መዛመድ ሳለ ሴጋ መምታት ኢየሱስ እየጠቀሰ የነበረው ነገር ነው ማለት የማይመስል ነበር፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ሴጋ መምታት ኃጥአት እንደሆነ የትም ሳይገልጽ ወደ ሴጋ መምታት የሚመሩ ድርጊቶች በኃጥአት የተሞሉ ስለመሆናቸው እና አለመሆናቸው ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ሴጋ መምታት ብዙውን ጊዜ የአመንዝራነት አስተሳሰብ፤ የወሲብ መቀስቀስ፤ እና/ወይም የወሲብ ቀስቃሽ ምስሎች ውጤት ነው፡፡ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባቸው እነዚህ ችግሮች ናቸው፡፡ የአመንዝራነት ኃጥአት፤ ግብረ-ገብነት ያጣን አስተሳሰቦችን፤ እና ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎች ከተዘነጉ እና ካሸነፉ ሴጋ መምታት መነጋገሪያ ይሆናል፡፡ ብዙ ሰዎች ሴጋ መምታትን በተመለከተ ከበደለኝነት ስሜት ጋር ይታገላሉ፤በእውነታው ወደ ድርጊቱ የሚመሩ ነገሮች በበለጠ ንስሐ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በሴጋ ጉዳይ ላይ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል የተወሰኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎች አሉ፡፡ ወደ ኤፈሶን ሰዎች 5፤3 “ ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ” እያለ ያውጃል፡፡ ሴጋ መምታት እንዴት ያን የተለየ ፈተና ማስተላለፍ እንደሚችል ማየት ከባድ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።” (1ኛ ቆሮንቶስ 10፤31)፡፡ ለአንድ ነገር ለእግዚአብሔር ክብርን መስጠት ካልቻልክ አታደርገውም፡፡ ግለሰቡ ድርጊቱ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንደሆነ በሙላት ካላመነ ኃጥአት ነው፤“ ከእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው።” (ወደ ሮሜ ሰዎች 14፤23)፡፡ በተጨማሪ ብልቶቻችን እንደተበዡ እና ለእግዚአብሔርም እንደሆኑ ልናስታውስ ይገባናል፡፡ “ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” (1ኛ ቆሮንቶስ 6፤19-20)፡፡ በብልቶቻችን በምናደርጋቸው ነገሮች ይህ ትልቅ እውነት ትክክለኛ አመለካከት አለው፡፡ በእነዚህ መርሆች እይታ ሴጋ መምታት ኃጥአት ነው የሚለው ድምዳሜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡ በግልጽ ሴጋ መምታት እግዚአብሔርን የሚያከብር አይደለም፤ ግብረ-ገብነት የማጣትን መልክም ሆነ እግዚአብሔር በብልቶቻችን ላይ ባለቤትነቱን የማስተላለፉን ፈተና አያስወግድም፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ሴጋ መምታት፤በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ኃጥአት ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries