settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የመንፈስ ቅዱስ ተአምራዊ ስጦታዎች ለዛሬም ናቸውን?

መልስ፤


በመጀመሪያ፣ መገንዘብ ጠቃሚ የሚሆነው፣ ይህ ጥያቄ እግዚአብሔር አሁንም ተአምራትን ያደርጋል አያደርግም ማለት አለመሆኑን ነው። እግዚአብሔር ዛሬ ሰዎችን አይፈውስም፣ ለሰዎች አይናገርም፣ እንዲሁም ተአምራዊ ምልክቶችንና ድንቆችን አያደርግም ማለት ሞኝነትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ጥያቄው ተአምራዊው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ፣ እሱም በቅድሚያ በ1ኛ ቆሮንቶስ 12-14 የተጠቀሰው፣ ዛሬም በቤተ ክርስቲያን ስለመደረጉ ነው። ይህም ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ለአንዱ ተአምራዊ ስጦታ ሊሰጠው ይችላልን የሚል ጥያቄ ለማንሣት አይደለም። ጥያቄው፣ መንፈስ ቅዱስ ዛሬም ቢሆን ተአምራዊ ስጦታዎችን ያከፋፍላልን የሚል ነው። ከሁሉም በላይ እኛ በጥቅሉ የምንገነዘበው መንፈስ ቅዱስ እንደ ፍቃዱ ስጦታዎችን ሊከፋፍል ነጻ መሆኑን ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡7-11)።

በሐዋርያት ሥራና በመልእክቶችም፣ አብዛኞቹ ተአምራት የተደረጉት በሐዋርያትና በእነሱ የቅርብ ረዳቶች ነው። ይህም የሆነበትን ምክንያት ጳውሎስ ነግሮናል፡ “በእርግጥ የሐዋርያነት ምልክት በመካከላችሁ በምልክትና በድንቅ ነገር በተአምራትም በሁሉ ትዕግሥት ተደረገ” 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡12)። እያንዳንዱ በክርስቶስ የሚያምን፣ ምልክቶችን፣ ድንቆችን፣ እና ተአምራትን የማድረግ ችሎታ ቢኖረው ኖሮ፣ ምልክቶች፣ ድንቆችና ተአምራት የሐዋርያነት መለያ ምልክት ሊሆኑ ባልቻሉ ነበር። ሐዋርያት ሥራ 2፡22 የሚነግረን ኢየሱስ “በተአምራት፣ በድንቆች፣ እና በምልክቶች” “ይታወቅ” እንደ ነበር ነው። በተመሳሳይም ሐዋርያት እንደ ቀና የእግዚአብሔር መልእክተኛ “የሚታወቁት” በሚፈጽሙት ተአምራት ነበር። ሐዋርያት ሥራ 14፡3 የሚገልጸው የወንጌል መልእክት “የሚጸናው” ጳውሎስና በርናባስ ባደረጉት ተአምራት ነበር።

1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 12-14 በቅድሚያ የሚገልጸው ርዕሰ ጉዳይ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ነው። ከዛ ጽሑፍ መነሻነት “ተራ” ክርስቲያኖች አንዳንዴ ተአምራዊ ስጦታዎች ይሰጧቸው ነበር (12፡8-10፣ 28-30)። ይህም እንዴት ተራ ስፍራ እንደነበረ አልተነገረንም። ከላይ በተማርነው መሠረት፣ ሐዋርያት “ይለዩ” የነበረው በምልክቶችና ድንቆች ነው፣ ይህም የሚመስለው ተአምራዊ ስጦታዎች “ለተራ” ክርስቲያኖች መሰጠታቸው በተለየ ሁኔታ እንጂ እንደ ደንብ አይደለም። ከሐዋርያትና ከቅርብ ተባባሪዎቻቸው በቀር አዲስ ኪዳን የትም ቦታ በተለየ መልኩ የመንፈስ ቅዱስን ተአምራዊ ስጦታዎችን የሚያደርጉ ሰዎች መኖራቸውን አይገልጽም።

ሌላው መገንዘብ ጠቃሚ የሚሆነው፣ ዛሬ እኛ እንዳለን የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን የተጠናቀረው መጽሐፍ ቅዱስ እንዳልነበራት ነው (2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17)። ስለሆነም፣ የትንቢት፣ የእውቀት፣ የጥበብ፣ ወዘተ… ስጦታዎች አስፈላጊ የነበሩት የጥንት ክርስቲያኖች፣ እግዚአብሔር ምን እንዲሠሩ እንደ ፈለገ እንዲያውቁ ነበር። የትንቢት ስጦታ፣ አማኞች አዲስ እውነትና ራዕይ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲያገኙ ያስችላቸው ነበር። አሁን የእግዚአብሔር መገለጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ተፈጽሟል፣ “መገለጣዊ” ስጦታዎች ከእንግዲህ አስፈላጊ አይሆኑም፣ ቢያንስ በአዲስ ኪዳን እንደነበሩት መጠን ባለ መልኩ።

እግዚአብሔር በየዕለቱ ሰዎችን በተአምራዊ መንገድ ይፈውሳል። እግዚአብሔር አሁንም ቢሆን ለእኛ ይናገረናል፣ ሊሰማ በሚችል ድምጽ ሆነ በአዕምሯችን፣ ወይም በመመሰጥና በስሜቶቻችን። እግዚአብሔር አሁንም ቢሆን አስገራሚ ተአምራትን፣ ምልክቶችን፣ እና ድንቆችን እንዲሁም አንዳንዴ እነዚህን ተአምራት በክርስቲያን በኩል ያደርጋል። ሆኖም፣ እነዚህ ነገሮች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ላይሆኑ ይችላሉ። የተአምራዊ ስጦታዎች ቀዳሚ ዓላማ፣ ወንጌል እውነት እንደነበረና ሐዋርያትም በትክክል የእግዚአብሔር መልእክተኞች መሆናቸውን ማረጋገጥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ተአምራዊ ስጦታዎች ተቋርጠዋል በግልጽ አይልም፣ ነገር ግን በአዲስ ኪዳን እንደተመዘገበው ባለ መልኩ ከአሁን ወዲያ እንደማይሆኑ መሠረቱን ያመላክታል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የመንፈስ ቅዱስ ተአምራዊ ስጦታዎች ለዛሬም ናቸውን?
© Copyright Got Questions Ministries