settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አንድ አምላክ አምላኪነት ሊረጋገጥ ይችላልን;?

መልስ፤


ሞሮቲዝም "monotheism" ከሁለት ቃላት የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ሞኖ›› "mono" አንድ "ብቸኛ" "single" እና "theism" "እምነት" ትርጉሙ "በእግዚአብሔር ማመን" የሚል ትርጉም አለው፡፡ በተለይም የአንድ አምላክነት አንድ ብቸኛ ፈጣሪ ነዋሪ እና ዳኛ በሆነው በእውነተኛው አምላክ ማመን ነው፡፡ ‹‹ሞኖቶኒዝም›› ከ "ሄኖቲዝም""henotheism" የተለየ ነው እሱም በብዙ አማልክት ጋር ከሁሉም ላይ ደግሞ የበለይ በሆነ አምላክ ጋር ያለ እምነት ነው፡፡ እሱም ደግሞ ‹‹ፖሊይቲይዝም›› ከአንድ በላይ አምላክ መኖሩን የማመን አምላኪነት ተቃውሞአል፡፡

ልዩ የሆነ መገለጥ (ቅዱሳት መጻሕፍት) ፤ የተፈጥሮ ራዕይ (ፍልስፍና) እንዲሁም ታሪካዊ ን የስው ልጅ ጥናት ጨምሮ ስለ አንድ አምላክ አምላኪነት ልዩ ልዩ ክርክሮች አሉ፡፡ እነዚህ በጥቂቱ ከዚህ በታች ተገልጸዋል እናም በዝርዝር እንደተገለጹ ሆናው መወሰድ የለባቸውም፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ መከራከሪያዎች ለሞኖቴይዝም ዘዳ — ዘዳግም 4፡35፡- ‹‹እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።›› (ዘዳግም 6 4) "እስራኤል ሆይ ስማ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው" ሚልኪያስ 2: 10፡- ‹‹ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? " 1 ቆሮንቶስ 8: 6:- ‹‹ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።" (ኤፌሶን 4 6)፡- " ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።" 1 ኛ ጢሞቴዎስ 2 : 5: — ‹‹አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤›› ያዕቆብ 2:19 "እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።"

በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ለብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገር ብቻ አንድ እግዚአብሔር እንዳለ ለመናገር በቂ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ያለ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያው የእግዚአብሔር መሆኑን ማረጋገጥ የሚችልበት መንገድ የለም፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ መሆኑን የሚያረጋግጠውን እጅግ በጣም አስተማማኝ ማስረጃ ስላለው እንዲህ ዓይነት አቋም አንድ አምላክ አምላኪነትን ሊረጋገጥ ይችላል፡፡ በተመሳሳይም ሌላው ክርክር ሊሆን የሚችለው የኢየሱስ ክርስቶስ እምነት እና ትምህርት የኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራዊ ልደት በህይወት እና በትንሣኤው ተዓምራዊነቱ እግዚአብሔር (ወይም ቢያንስ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው) ያረጋገጠ እምነትና አስተምህሮ ነው፡፡ እግዚአብሔር አይዋሽም ወይም ሊታለል አይችልም፤ ስለዚህ ኢየሱስ ያምንና ያስተማረው የነበርው እውነት ነው፡፡ ስለዚህ ሞኖቴይዝም ኢየሱስ ያምንና ያስተማረው የነበረው እውነት ነው፡፡ ይህ ሙግት ስለቅዱስ ቃሉ እና ስለክርስቶስ ምንም የማያውቋ ሰዎች በጣም የሚገርም ላይሆን ይችላል ግን ይህን ለሚያውቅ ሰው ጥንካሬውን ለመጀመር ይህ ጥሩ ቦታ ነው፡፡

ስለሞኖይቲይዝም ያሉ ታሪካዊ ሙግቶች በታዋቂነት ላይ የተመሠረቱ ክርክሮች በጥርጣሬ ተጠርጥረው ይገኛሉ፤ ነገር ግን አንድ አምላክ አንድነት በዓለም ሃይማኖቶች ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንደነበረው አስገራሚ ነው፡፡የሃይማኖታዊ የዝግመተ ለውጥ ጽንሰ-ሐሳብ እድገት ከጠቅላላው በዝግመተ ለውጥ እውነታ ላይ ሲታይ የቀድሞውን የሃይማኖት ልደት ደረጃዎች የሚያመለክቱ "ጥንታዊ" ባህሎች የሚያዩ የዝግመተ ለውጥ አንትሮፖሎጂ ቅድመ-ግምት ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ የዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ላይ ያሉ ችግሮች ብዙ ናቸው 1) የሚያብራራው የእንደዚህ አይነት እድገት ታይቶ አያውቅም፤ በየትኛውም ባሕል ውስጥ ስለ አንድ አምላክ አንድ ዓይነት አዝማሚያ ያለ አይመስልም፤ እውነቱን ግን ተቃራኒው ይመስላል 2) የአንትሮፖሎጂ ዘዴ "ጥንታዊ" የሚለው ትርጉም ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ነገር ግን በተወሰነ ባህል ውስጥ ብዙ አካላት እንዳሉበት ይህ እጅግ ከፍተኛ መስፈርት ነው 3) የተለመዱ ደረጃዎች በአብዛኛው ጠፍተዋል ወይም ተዘለዋል 4) በመጨረሻም ብዙዎቹ በዙ አማልክት አምላኪዎች ባህሎች ቀደም ባሉት ጊዜያት የእድገት አማራጮችን እንደሚያመለክቱ ያሳያሉ፡፡

እኛ የምናገኘው ነገር አንድ አምላክ ተባዕታይ ሰማያዊ ህይወት ያለው ታላቅ እውቀትና ኃይል ያለው ዓለምን የፈጠረ እኛ ተጠያቂ የምንሆንበት የሥነ-ምግባር ደራሲ እና እኛ ያልታዘዝ እና በዚህም ምክንያት የተወገፈ ግን ግን የማስታረቅ መንገድ አቅርቧል ሁሉም ሃይማኖቶች ማለት ከዚህ በፊት በተወሰነ ጊዜ ይህን አምላክ ልዩነት ያደርጉታል በዚህ ምክንያት አብዛኞቹ ሃይማኖቶች በአንድ አምላክ አምላኪነት ላይ ተሰማርተው ወደ "ጣዖታት" ወደ መናፍስታዊነት እና ወደ አስማሚነት ያሸጋጉ አይመስሉም — በተቃራኒው አይደለም (እስልምና እጅግ በጣም ያልተለመደ ነገር ነው) በዚህ እንቅስቃሴም ቢሆን ብዙ አማልክት አምላኪነት በአዶአዊ አሀድነት ወይም በሀይኖታዊነት የተሞላ ነው ይህ የአምልኮ ጣዖታትን እንደ አማላጅ አድርጎ የሚይዝ የአማልክት ጣዖታዊ ሃይማኖት ነው አናሳዎቹ አማልክት እንደ አማላጅ ሆነው ይሠራሉ

የፍልስፍና / ሥነ-መለኮታዊ ተቃርኖዎች ለሞኖቴይዝም — በርካታ ፍልስፍናዊ ክርክሮች አሉ፤ አንድ በቻነው ያለው ብሎ ለማለት የማያስችሉ ብዙ የፍልስፍና ሃሳቦች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ስለ ተጨባጭ ሁኔታ ከሚገልጠው ይልቅ ስነ-ቁሳዊ አቋም አውነታ ላይ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ በዚህ አጭር ጽሑፍ ውስጥ እንደዚህ ያለውን የፍልስፍና እውቀት ለማጥናት እና ለእነዚህ መሰረታዊ የሞኖቴይዝም አቋሞት መሟገት የማይቻል ነው ግን በእርግጠኝነት ማረፍ ይቻላል ጠንካራ የሆኑ የፍልስፍና እና ስነመለኮታዊ መሰረቶች ስለዚህ እውነት ለዘመናት ወደ ኋላ ተመልሶ ማየት ይቻላል፤ (አብዘኛዎቹ ግልል እምነት መረጃ ናቸቸው) በአጭሩ እንግዲ እነዚህ ናቸው ለማጥናት እንድንመርጥ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1ከአንድ በላይ የሆነ አምላክ ከነበረ ዪኒቨርስ ስነፍጥረቱ ከፈጣሮዎች ብዛት የተነሳ ዝብርቅርቅ ይሆን ነበር፤ ግን ዝብርቅርቅ አይደለም እንገዲያውስ ያለው አንድ አምላክ ነው፡፡

2 እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ ስለሆነ ሌላ ሁለተኛ አምላክ ሊኖር አይችልም ወይንም በተወሰነ መልኩ የተለያዩ መሆን አለባቸው እና ሙሉ ከሆነው ፍጹምነት የተለየ ያነሰ ደግሞ እግዚአብሔር ሊሆን አይችልም፡፡

3 እግዚአብሔር በህልውናው ፍጹም እስከሆነ ድረስ ክፍልፋይ ሊኖረው አይችልም (ክፍል ያለው ወሰን የሌለው ሊሆን አይችልም)፡፡ የእገዚአብሔር መኖር የእርሱ ክፋይ ካልሆነ (የትኛው ህልውና ያለው ሊሆን ነው ወይም ላይሆን ነው) ስለዚህ ወሰን የሌለው ህልውና ሊኖረው ይገባል፡፡ እንገዲያውስ ሁለት ወሰን የሌለው አካል ሊኖሩ አይችሉም አንዱ ከሌላው የሚለይ መሆን አለበት፡፡

አንድ ሰው ከዚህ ብዙዎቹ የአማልክትን መከፋፈል ሊከራከር ሊፈልግ ይችላል መልካም ነው፡፡ ሆኖም ይህ በእግዚአብሔር ቃል ውሸት መሆኑን እናውቃለን፤ ጽንሰ ሃሳቡ ባሩሱ ምንም ችግር የለውም፡፡ በሌላ ቋንቋ እግዚአብሔር ለአማልክቶች ክፍል ደረጃን ሰርቶአል፤ ይህ ላለማድረጉ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ አድርጎ ቢሆን አማልክቶች ውስኖች ይሆኑ ነበር የተፈጠሩ ነገሮችም እንደመልአክት ሊሆኑ ይችላሉ (መዝ 82) ይህ ሌላ መንፈሳዊ አካል ሊኖር አይችልም የሚለውን ሞኖቴይዝምን የሚጎዳ አይደለም፤ ከአንድ አምላክ በላይ ሊኖር አይችልም፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አንድ አምላክ አምላኪነት ሊረጋገጥ ይችላልን;? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries