ጥያቄ፤
ስለ ኢየሱስ ለመስማት ጨርሰው ዕድል ያላገኙት ሰዎች ምን ይሆናሉ? እግዚአብሔር ስለ እርሱ ጨርሶ ሰምቶ የማያውቀውን ሰው ይኮንነዋልን?
መልስ፤
ሰዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር ተጠያቂነት አለባቸው፤ ስለ “እሱ ሰሙም ሆነ አልሰሙ።” መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን፣ እግዚአብሔር በግልጽ ራሱን ገልጿል፣ በተፈጥሮ (ሮሜ 1፡20) እንዲሁም በሰዎች ልብ ውስጥ (መክብብ 3፡11)። ችግሩ የሰው ዘር ኃጠአተኛ መሆኑ ነው፤ እኛ ሁላችንም ይህንን የእግዚአብሔር እውቀት ትተን በእሱ ላይ እናምፃለን (ሮሜ 1፡21-23)። በእግዚአብሔር ጸጋ ባይሆን ኖሮ ሁላችንም ለልባችን የኃጢአት መሻት በተሰጠን ነበር፣ ከእሱ መራቅ የቱን ያህል ጥቅመ ቢስና የመከራ ሕይወት እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ይፈቅዳል። ይህን የሚያደርገው ቀጣይነት ባለው መልኩ እሱን የማይቀበሉትን ነው (ሮሜ 1፡24-32)።
እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ጉዳዩ ጥቂት ሰዎች ስለ እግዚአብሔር አለመስማታቸው አይደለም። ይልቁን፣ ችግሩ የሰሙትን እንዲሁም በተፈጥሮ ያዩትን አለማመናቸው ነው። ዘዳግም 4፡29 እንዲህ ያውጃል፣ “ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።” ይህ ቁጥር ጠቃሚ መርሕ ያስተምራል— ማንም እግዚአብሔርን በእውነት ከፈለገ ያገኘዋል። አንድ ሰው በእውነት እግዚአብሔርን ለማወቅ ከፈለገ፣ እግዚአብሔር ራሱን ይገልጽለታል።
ችግሩ “አስተዋይም የለም አንድስ እንኳ፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም” እንደተባለ ነው (ሮሜ 3፡11)። ሰዎች በተፈጥሮ የተሰጣቸውንና በልባቸው ያለውን የእግዚአብሔር እውቀት ንቀው፣ በምትኩ በራሳቸው የተፈጠረውን “ጣዖት” ለማምለክ ወሰኑ። የእግዚአብሔርን ፍትሐዊነት መከራከር ሞኝነት ነው፣ ማንም ፈጽሞ የክርስቶስን ወንጌል የመስማት ዕድል ሳያገኝ ወደ ገሃነም እንደሚጥለው ያለ። ሰዎች ለእግዚአብሔር ኃላፊነት አለባቸው፣ እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ለገለጠላቸው ነገር። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ሰዎች ይሄንን እውቀት እንዳልተቀበሉት ነው፣ ስለሆነም እግዚአብሔር ወደ ገሃነም ቢጥላቸው ፍትሐዊ ነው።
ፈጽመው ስላልሰሙት ዕጣ ከመከራከር ይልቅ፣ እኛ እንደ ክርስቲያን፣ በርግጠኝነት ይሰሙ ዘንድ የሚቻለንን ሁሉ ማድረግ አለብን። እኛ የተጠራነው ወንጌልን ለሕዝቦች ሁሉ እንድናሰራጭ ነው (ማቴዎስ 28፡19-20፤ ሐዋርያት ሥራ 1፡8)። ሰዎች በተፈጥሮ የተገለጠላቸውን የእግዚአብሔርን እውቀት እንዳልተቀበሉት እናውቃለን፣ እናም ይሄ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የመዳን መልካም የምስራች እናውጅላቸው ዘንድ ያነሣሣናል። የእግዚአብሔርን ጸጋ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያለውን በመቀበል ብቻ ሰዎች ከኃጢአታቸው ሊድኑና ከእግዚአብሔር ለዘላለም ከመለየት ሊጠበቁ ይችላሉ።
ወንጌልን ፈጽመው ያልሰሙት ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት ይጠብቃቸዋል ብለን የምናስብ ከሆነ በአስፈሪ ችግር ውስጥ እንሆናለን። ወንጌልን ፈጽመው ያልሰሙ ሰዎች የሚድኑ ከሆነ፣ አመክኖአዊ የሚሆነው፣ እኛ እርግጠኛ መሆን ያለብን ማንም ሰው ፈጽሞ ወንጌልን አለመስማቱን ነው። እኛ ማድረግ የምንችለው የከፋው ነገር፣ ወንጌልን ከሰውየው ጋር መካፈልና እንዳይቀበለው ወይም እንዳትቀበለው ማድረግ ብቻ ነው። እንደዛ የሚሆን ከሆነ እሱ ወይም እሷ ይኮነናሉ። ወንጌልን ያልሰሙ ሰዎች ሊፈረድባቸው ይገባል፣ አለበለዚያ ለወንጌላዊነት የሚያነሣሣ ነገር አይኖርም። ሰዎች ለምን ወንጌልን ባለመቀበል እና ራሳቸውን በመኮነን የሚሆነውን ጉዳት ይይዛሉ፣ እነሱ ቀደም ብለው ወንጌልን ፈጽመው ባለመስማታቸው ምክንያት የሚድኑ ከሆነ?
English
ስለ ኢየሱስ ለመስማት ጨርሰው ዕድል ያላገኙት ሰዎች ምን ይሆናሉ? እግዚአብሔር ስለ እርሱ ጨርሶ ሰምቶ የማያውቀውን ሰው ይኮንነዋልን?