ጥያቄ፤
እንዴት ነው ወደ ሲኦል የማልሄደው?
መልስ፤
ወደ ሲኦል ለመሄድ ከምታስበው በላይ ቀላል ነው፡፡ አንዳንዶች ወደ ሲኦል ላለመሄድ አስሩን ትዕዛዛት መጠበቅ እንዳለባቸው ያስባሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ አንዳንድ ስርዓቶችን መፈጽም ወደ ሲኦል ላለመሄድ አስፈላጊ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ አንዳንዶችም ወደ ሶኦል እንሂድ አንሂድ ማወቅ አይቻልም ይላሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ትክክል አይደሉም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እዴት አንድ ሰው እንዴት ወደ ሲኦል ሊሄድ እደንማይችል ይናገራል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ሲኦል እንዴተ ያለ አስከፊና አስፈሪ ቦታ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ሲኦል ‹‹ዘላለማዊ እሳት›› ተብሎ ተገልጾአል (ማቲ 12፡2) አሳቱ የማይጠፋበት ቦታ (ማቲ 3፡12) የእፍረት እና የጉስቁልና ስፍራ (ዳን 12፡2) አሳቱ የማይጠፋበት ስፍራ (ማር 9፡44-49) እና የዘለአለም ጥፋት (2ተሰ 1፡9) ራዕ 20፡10 የእሳት ባህር ኃጢያተኞች ‹‹ከዘለአለም እስከ ዘለአለም የሚቃጠሉበት›› (ራዕ 20፡10) እውነት ነው ሲኦል ልናስወግደው ልናመልጠው የምንችለው ስፍራ ነው፡፡
ሲኦል ያለው የት ነው ለምንድን ነው የሲኦል መኖር ያስፈለገው? መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለሰይጣን እና ለወደቁ መላዕክት በእግዚአብሔር ላይ ካመጹ በኋላ ‹‹እንዳዘጋጀው›› ይነግረናል (ማቲ 25፡41)፡፡ እግዚአብሔር ምህረቱን የሚቃወሙ ከሰይጣን እና ከክፉ መላዕክት ጋር ተመሳሳይ የዘለአለም ቅጣት ይቀበላሉ፡፡ ለምንድን ነው ሲኦል ያስፈለገው? ኃጢያትን የሚያደርጉ እግዚአብሔርን ይቃወማሉ (መዝ 51፡4) እግዚአብሔር ዘላለማዊ ማንነት ያለው እንደመሆኑ ዘላለማዊ ቅጣት ብቻ ነው በቂ የሚሆነው፡፡ ሲኦል እግዚአብሔር ቅዱስ የሚሆንበት እና የጽድቅ የፍትህ ስራ የሚደረግበት ነው፡፡ ሲኦል እግዚአብሔር ኃጢያትን የሚቀጣበት እና እርሱን የሚቃወሙትን የሚቀጣበት ስፍራ ነው፡፡ እኛ ኃጢያተኞች እንደሆንን መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ያደርግልናል (መክ 7፡20? ሮሜ 3፡10-23) ስለዚህ ሁላችንም ሲኦል ይገባናል፡፡
ስለዚህ እንዴት ነው ወደ ሲኦል ላንሄድ የምንችለው? ገደብ የሌለው እና ዘላለማዊ ቅጣት ብቻ የሚበቃው ከሆነ ዘላለማዊ ዋጋ የግድ መከፈል አለበት፡፡ መለኮት በክርስቶስ ኢየሱስ ስጋ መልበስ ሰው ሆኖአል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖአል ፈውሶናል ግን ከላይ ያየናቸው እነዛ ነገሮች የእግዚአብሔር እቅድ አይደሉም፡፡ ቃል ስጋ ሆነ (ዮሐ 1፡1?14) ስለዚህም ሊሞትልን ቻለ፡፡ ኢየሱስ በስጋ የተገለጠ መለኮት ነው በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ እንደ እግዚአብሔር የእርሱ ቅጣት ሞትም ዋጋው ዘላለማዊ ስለሆነ የኃጢያትን መሉ ወጋ ይከፍላል (1ዮሐ 2፡2) እግዞአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛችን አድርገን እንድንቀበል ጋብዞናል፤ የእርሱን ሞት የኃጢያታችን ትክክለኛ ዋጋ አድርገን እንድንቀበል፡፡ እግዚአብሔር በክርስቶስ የሚያምን (ዮሐ 3፡16) እርሱ ብቻ እንደሚያድን የሚያምን (ዮሐ 14፡16) እርሱ ይድናል ያም ማለት ወደ ሲኦል አይሄድም፡፡
እግዚአብሔር ማንም ወደ ሲኦል እንዲሄድ አይፈልግም (2ጴጥ 3፡9) እግዚአብሔር ለዚ ነው የመጨረሻውን ፍጹሙን እና የሚበቃውን መስዋዕት በእኛ ፈንታ የከፈለው፡፡ ወደ ሲኦል መሄድ የማትፈልግ ከሆነ ኢየሱስን የግል መድኃኒትህ አድርገሀፍ ተቀበል፡፡ የዚህን ያክል ቀላል ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ኃጢያተኛ መሆንህን እንደተገነዘብክ ንገረው ሲኦል ይገባህ እንደነበረም እንዲሁ፡፡ ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ሊያድንህ እንደሚችል እንደምታምን ንገረው፡፡ እግዚአብሔርን ስላዘጋጀልህ ድኅነት ከሶኦልም እንዳዳነህ አመስግነው፡፡ በእምነት ብቻ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያድን ማመን በዚህ መንገድ ነው ወደ ሲኦል መሄድን የምታስወግደው!
English
እንዴት ነው ወደ ሲኦል የማልሄደው?