settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የድኅነት ጸሎት ምንድን ነው?

መልስ፤


ብዙ ሰው ይጠይቃሉ? ‹‹ደኅነትን ሊያረጋግጥልኝ የሚችል የምጸልየው ጸሎት ይኖራል?›› አንድ ነገር ማስታወስ ያስፈልጋል ድኅነት የሆነ ጸሎትን በማቅረብ የሆኑ ቃላትን በማነብነብ አይገኝም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በየትም ስፍራ የሆነ ጸሎት በማቅረብ ደኅነት እንደሚገኝ አያስተምርም፡፡ ጸሎትን መድገም ደኅነትን የማግኛ መንገድ ሊሆን አይችልም፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊው የድኅነት መንገድ በክርስቶስ ኢየሱስ ማመን ነው፡፡ ዮሐ 3፡16 ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።›› ደኅንነት የሚገኘው በእምነት ነው፡፡ኤፌ 2፡8 ኢየሱስን አዳኝ አድርጎ በመቀበል (ዮሐ 1፡12)? ኢየሱስን ብቻ በመታመን (ዮሐ 14፡16?ሥራ 4፡12) ጸሎትን በመድገም አይደልም፡፡

መትሃፍ ቅዱሳዊው የድኅነት መልዕክት ምንጊዜሜ ቢሆን ቀላልና ግልጽ ሲሆን ሁልጊዜም አስደናቂ ነው፡፡ ሁላችንም እግዚአብሔርን በድለናል (ሮሜ 3፡23)፡፡ ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ማንም ሰው አንዴም ሳይበድል ደህንነት ሊያገኝ አይችልም (መክ 7፡20)፡፡ በኃጢያታችን ምክንያት ሁላችን ፍርድ ከእግዚአብሔር ዘንድ አለብን ይህውም ሞት (ሮሜ 6፡23)፡፡ በኃጢያታችን ምክንያት ፍርድ ይገባናል በራሳችን በእግዚአብሔር ፊት ትክክል ለመሆን ምንም ልናደርግ አንችልም፡፡ እርሱ ለእኛ ባለው ፍቅር መለኮት በክርስቶስ ኢየሱስ ሰው ሆነ፡፡ ኢየሱስ ፍጹም የሆነውን ህይወት በመኖር እውነትን አስተማረ ሆኖም ግን ሰዎች ኢዩስን ተቃወሙት ኢየሱስን ወደ ሞት ወስደው ሰቀሉት፡፡ በዛ ንጸውን ሰው የመግደል አሰቃቂ የግድያ ተግባር የደኅንነታችን ስራ ተፈጸመ፡፡ ኢየሱስ በእኛ ፈንታ ሞተ፡፡ የኃጢያታችንን ፍርድ በራሱ ላይ አደረገው (2ቆሮ 5፡21)፡፡ ኢሱስ ከሙታን ተነስቶአል (1ቆሮ 15) የእርሱ የኃጢያት ክፍያ በቂ ነበር እርሱ ኃጢያትና ሞትን አሸንፎአል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት እግዚአብሔር ደኅነትን ሰጠን በነጻ ሰጠን፡፡ እግዚአብሔር ሁላችንንም ለንሰሃ ጠርቶናል (ሥራ 17፡30)፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የመስዋዕትነት ስራ ሙሉ በሙሉ ማመን (1ዮሐ 2፡2)፡፡ ድኅነት የተገኘው የእግዚአብሔርን ስጦት በመቀበል እንጂ የሆነ ጸሎትን መጸለይ አይደለም፡፡

አሁን ያማለት ግን ድኅነትን ለመቀበል ጸሎት አያስፈልግም ማለትን ግን አይደለም፡፡ ወንጌልን ከተረዳን እውነት መሆኑን ካመንን እና ኦሲስም የደኅንነት መንገድ አድርገን ከተቀበልን እምነታችንን በጸሎት መገለጽ ተገቢ እና ትክክለኛ ነገር ነው፡፡ እግዘአብሔርን በጸሎት መገናኘት ኢየሱስ ክርስቶስነ ከመቀበል በማረፈ ሙሉ ሙለ እንደ አማኝ ወደ ማመን ሊወስድ ይቻላል፡፡ ጸሎት በደኅንነት ሙሉ በሙሉ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን ሊወስድ ይችላል፡፡

እንደገና ድኅነትን መጸሎት በማነብነብ ላይ አለመመስረት ወና እና በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ጸሎትን መደጋገም አያድንም! በኢየሱስ ክርስቶሰ የሚገኘውን ደኅነት ለመቀበል ከፈለግክ እምነትህን በእርሱ ላይ አድርግ፡፡ የእርሱ ሞት ለኃጢያትህ የሚበቃ መስዋዕት እንደሆነልህ እመን፡፡ ሙሉ በሙሉ እምነትህን በእርሱ ላይ ጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የደኅንነት መንገድ ይህ ነው፡፡ ኢየሱስን የግል አዳኝህ አድርገህ ከተቀበልክ በማንኛውም መንገድ ጸሎትን ጸልይ፡፡ ኢየሱስን ምን ያህል እንደምታመሰግነው ተናገር፡፡ እግዚአብሔርን ስለፍቅር መስዋዕቱ አመስግነው፡፡ ኢየሱስ ስለኃጢያትህ እንደሞተልህ ስለሞተልህ እና ድኅነትን ስላዘጋጀልህ አመስግነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው ድኅነትና ጸሎት ግንኙነት ይህው ነው፡፡

English


ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ
የድኅነት ጸሎት ምንድን ነው?
© Copyright Got Questions Ministries