ጥያቄ፤
ቅድመ ሚሊኒየማዊነት ምንድነው?
መልስ፤
ቅድመ ሚሊኒየማዊነት ማለት የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከሚሊኒማዊ መንግሥቱ ቀደም ብሎ ይሆናል የሚል አመለካከት ነው፣ ያም ሚሊኒየማዊ መንግሥት በጥሬው የ1000 ዓመት የክርስቶስ ግዛት በምድር ላይ ነው። ቅዱስ ቃሉ ላይ ስለ ፍጻሜ ዘመን ሁነቶች የሚገልጹትን ምንባቦች ለመረዳትና ለመተርጎም፣ ሁለት ነገሮችን በግልጽ መረዳት ያስፈልጋል፡ ቅዱስ ቃሉን ባግባቡ መተርጎሚያ መንገድ እና በእስራኤል (አይሁድ) እና በቤተ-ክርስቲያን (በኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም አማኞች አካል) መካከል ያለው ልዩነት።
በመጀመሪያ፣ ቅዱስ ቃሉን ባግባቡ የመተርጎሚያ መንገድ የሚጠይቀው፣ ቅዱስ ቃሉ የሚተረጎመው በዐውደ-ጽሑፉ አኳያ ቋሚ በሆነ መንገድ ነው። ማለትም፣ ምንባቦች መተርጎም የሚኖርባቸው ለተጻፈላቸው ታዳሚዎች ባለው ሁኔታ ነው። ደራሲውን፣ ታሳቢ ታዳሚዎቹን፣ እና የእያንዳንዱን ምንባብ ታሪካዊ ዳራ ማወቅ ለተርጓሚው ከበድ ይላል። ታሪካዊና ባህላዊ መቼቶቹ የምንባቡን ትክክለኛ ፍቺ ዘወትር ይገልጻሉ። ደግሞም ቅዱስ ቃሉ ቅዱስ ቃሉን እንደሚተረጉመው ማስታወስ ጠቃሚ ነው። ማለትም፣ ምንባቡ ርዕሱን ወይም ፍሬ ሐሳቡን ዘወትር ስለሚይዝ ነው፣ በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የተጠቀሰውን። ደግሞም እነዚህን ሁሉ ምንባቦች እርስ በርሳቸው መተርጎም ጠቃሚ ነው።
በመጨረሻ፣ እጅግ አስፈላጊ በሆነ መልኩ፣ ምንባቦች ዘወትር መወሰድ የሚኖርባቸው በተለመደው፣ በመደበኛው፣ ግልጽ በሆነው፣ ጥሬ (እማሬያዊ) ፍቺ ነው፣ የምንባቡ ዐውደ-ጽሑፍ በባሕርዩ ፍካሬያዊ ፍቺ እስካላመለከተ ድረስ። እማሬያዊ ትርጉም በጥቅም ላይ የዋሉትን የዘይቤአዊ ፍችዎች መገኘት አያጠፋቸውም። ይልቁንም፣ ተርጓሚው ዘይቤአዊ ቋንቋን ወደ ምንባቡ ትርጉም እንዳያስገባ ያደርገዋል፣ ለእዛ ዐውደ-ጽሑፍ ተገቢ እስካልሆነ ድረስ። “እጅግ ጥልቅ መንፈሳዊ” ፍቺ ፈጽሞ አለመፈለግ ዋነኛ ነገር ነው፣ ከቀረበው በላይ። ምንባብን መንፈሳዊ ማድረግ አደገኛ ነው፣ ምክንያቱም የቅዱስ ቃሉን ትክክለኛ የትርጓሜ መሠረት ወደ አንባቢው ሐሳብ ስለሚያዞረው። ከዚያም፣ ምንም ተጨባጭ የትርጓሜ መለኪያ ላይኖር ይችላል፤ በምትኩም፣ ቅዱስ ቃሉ እያንዳንዱ ግለሰብ እንዳፈቀደው በገዛ ራሱ እይታ ፍቺ የሚሰጠው ይሆናል። ሁለተኛ ጴጥሮስ 1፡20-21 ያስታውሰናል፣ “በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፍቃድ አልመጣምና፣ ዳሩግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።”
ይህን መሰሎቹን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ መርሖዎች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ፣ የግድ መታየት ያለበት እስራኤል (የአብርሃም የሥጋ ዝርያዎች) እና ቤተ-ክርስቲያን (ሁሉም የአዲስ ኪዳን አማኞች) ሁለት የተለያዩ ቡድኖች ናቸው። እስራኤልና ቤተ-ክርስቲያን የተለያዩ ቡድኖች መሆናቸውን መገንዘብ ዋነኛ ነገር የሚሆንበት ምክንያት፣ ይህንን በተሳሳተ ከተረዳነው ቅዱስ ቃሉንም በተሳሳተ ስለምንረዳው ነው። በተለይም፣ የተዛባ ትርጓሜ አዝማሚያ ለእስራኤል በተሰጡት የተስፋ ቃሎችን በሚገልጹት ምንባቦች ላይ (በሁለቱም፣ በተፈጸሙትና ባልተፈጸሙት)። እነዚህ ተስፋዎች በቤተ-ክርስቲያን ላይ ተግባራዊ መሆን የለባቸውም። የምንባቡ ዐውደ-ጽሑፍ ለማን መጻፉን እንደሚወስነው አስታውሱ፣ እንዲሁም እጅግ የተሻለውን ትክክለኛ ትርጓሜ ያመለክታል።
እነዚህን ጽንሰ-ሐሳቦች በመያዝ የተለያዩ የቅዱስ ቃሉን ምንባቦች መመልከት እንችላለን፣ እነርሱም ቅድመ ሚሊኒየማዊነት አመለካከት የሚፈጥሩትን። ዘፍጥረት 12፡1-3፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፣ ‘ከአገርህ፣ ከዘመዶችህም፣ ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔም ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፣ እባርክሃለሁ፣ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።’”
እግዚአብሔር ለአብርሃም እዚህ ቃል የገባለት ሦስት ነገሮችን ነው፡ አብርሃም ብዙ ዝርያዎች ይኖሩታል፣ ይህ ሕዝብም ርስት ይኖረዋል፣ ይኖርበታልም፣ እንዲሁም ሁለንተናዊ የሆነ በረከት ለሰው ልጆች ሁሉ ይሆናል፣ ከአብርሃም ዘር (አይሁድ)። ዘፍጥረት 15፡9-17፣ እግዚአብሔር ኪዳኑን ከአብርሃም ጋር ያደርጋል። ይህ በተደረገበት መንገድ፣ እግዚአብሔር ብቸኛውን ኃላፊነት በራሱ ይወስዳል። ያ ማለትም፣ አብርሃም ምንም አያደርግም፣ ማድረግ ሲኖርበት ያላደረገው የለም፣ እግዚአብሔር ያደረገውን ኪዳን ዋጋ እንዳይኖረው ለማድረግ። ደግሞም በዚህ ምንባብ፣ ለምድሩ ወሰኖች ተደርገው ነበር፣ አይሁድ ለሚኖሩበት። ለተብራራው የወሰኖቹ ዝርዝር ዘዳግም 34 ተመልከት። ሌሎች ከተስፋ ምድር ጋር በተያያዘ ያሉት ምንባቦች ዘዳግም 30፡3-5 እና ሕዝቅኤል 20፡42-44።
2 ሳሙኤል 7፡10-17 ላይ እግዚአብሔር ለንጉሥ ዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን እንመለከታለን። እዚህ፣ እግዚአብሔር ለዳዊት ቃል የገባለት ዝርዮች እንደሚኖሩት ነው፣ ከእነዚያ ዝርዮቹም እግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግሥት ያጸናለታል። ይህ የሚያመለክተው የክርስቶስን አገዛዝ ነው፣ በሚሊኒየም ጊዜና ለዘላለም። ጠቃሚ የሚሆነው ይህ ተስፋ በጥሬው መፈጸም እንዳለበትና ገና እስካሁን እንዳልሆነ ነው። አንዳንዶች የሚያምኑት የሰሎሞን አገዛዝ የዚህ ትንቢት እማሬያዊ ፍጻሜያዊ እንደሆነ ነው፣ ነገር ግን እዚያ ላይ ችግር አለ። ሰሎሞን የገዛው ግዛት አሁን በእስራኤል የተያዘ አይደለም፣ አሁንም ሰሎሞን በእስራኤል ላይ እየገዛ አይደለም። እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባለትን ቃል አስታውሱ፣ ማለትም ዝርዮቹ ምድሩን ለዘላለም እንደሚወርሱ። ደግሞም፣ 2 ሳሙኤል 7 የሚለው፣ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚገዛ መንግሥት እንደሚመሠርት ነው። ሰሎሞን ለዳዊት የተገባው ቃል ፍጻሜ ሊሆን አልቻለም። ስለዚህ፣ ይህ ተስፋ ገና የሚፈጸም ነው።
እንግዲህ፣ ይሄንን ሁሉ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ራዕይ 20፡1-7 ላይ የተመዘገበውን መርምሩ። አንድ ሺው ዓመት፣ እሱም በዚህ ምንባብ ላይ በተደጋጋሚ የተጠቀሰው የሚጎዳኘው ከክርስቶስ 1000 ዓመት እማሬያዊ አገዛዝ ጋር ነው፣ በምድር ላይ። ለዳዊት የተነገረው ተስፋ፣ ገዥን በተመለከተ በእማሬያዊ ፍቺ መጸፈም የሚገባው ሲሆን ገና እስካሁን አልሆነም። ቅድመ ሚሊኒየማዊነት ይሄንን ምንባብ የሚመለከተው እንደ ቀጣዩ ተፈጻሚ ተስፋ ነው፣ ክርስቶስ በዙፋኑ ላይ እንደሚሆን። እግዚአብሔር ሁኔታዊ ያልሆኑ ቃል ኪዳናት ከሁለቱም ከአብርሃምም ሆነ ከዳዊት ጋር አድርጓል። እነዚህ ኪዳናት አንዳቸውም ቢሆኑ በሙሉ ወይም በቋሚነት አልተፈጸሙም። የክርስቶስ እማሬያዊ፣ አካላዊ አገዛዝ ብቸኛው መንገድ ነው ኪዳናቱ ሊፈጸሙበት የሚችሉት፣ እግዚአብሔር እንደዚያ እንዲሆኑ እንዳለው።
በቅዱስ ቃሉ ላይ እማሬያዊ የትርጓሜ ዘዴ መጠቀም ውጤቱ አናሳ ዕንቆቅልሾችን አንድ ላይ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ሁሉም የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች፣ ስለ ኢየሱስ የመጀመሪያ ምጽአት የተነገሩት በጥሬው ተፈጽመዋል። ስለዚህ፣ ስለ ዳግም ምጽአቱ የተነገሩት ትንቢቶች ደግሞ በጥሬው እንደሚፈጸሙ እንጠብቃለን። ቅድመ-ሚሊኒየማዊነት ብቸኛው ሥርዓት ነው፣ ስለ እግዚአብሔር ኪዳናትና የፍጻሜ ዘመን ትንቢት እማሬያዊ ፍች የሚስማማ።
English
ቅድመ ሚሊኒየማዊነት ምንድነው?