settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ራሴን እንዴት ለጋብቻ ማዘጋጀት እችላለሁ?

መልስ፤


ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያ ራስን ለጋብቻ ማዘጋጀት፣ ቍጠኝነትን ለሚሻ ሕይወት እንደ መዘጋጀት ያለ ነው። ዳግም እንደተወለዱ አማኞች ሁሉንም የሕይወታችንን ገጽታዎች መግዛት ያለባቸው መርሖዎች አሉ፡ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ እና በፍጹም ሐሳብህ ውደድ” (ማቴዎስ 22፡37)። ይህ የዝም ብሎ ትዕዛዝ አይደለም። እሱ እንደ አማኞች ለሕይወታችን ማዕከላዊ ነው። እሱ እንድናተኩር የተመረጠ ነው፣ በእግዚአብሔር እና በቃሉ ላይ፣ በፍጹም ልባችን፣ ነፍሳችንም ሆነ ሐሳባችን እሱን በሚያስደስቱት ነገሮች እንዲሞላ።

በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት፣ ሌሎቹን ግንኙነቶች ሁሉ ወደ ጋራ አስተሳሰብ ያመጣ ነው። የጋብቻ ግንኙነት የተመሠረተው በክርስቶስና በእርሱ ቤተ-ክርስቲያን ማሳያ (ሞዴል) ነው (ኤፌሶን 5፡22-33)። እያንዳንዱ የሕይወታችን ገጽታ የሚገዛው እንደ አማኝ ባለን ቁርጠኝነት ነው፣ በጌታ ትእዛዛትና ሐሳብ መሠረት። ለእግዚአብሔርና ለቃሉ ያለን ታዛዥነት እግዚአብሔር የሰጠንን በጋብቻና በዓለም ላይ ያለንን ሚና እንድንጫወት ያበቃናል። የእያንዳንዱ ዳግም-ተወላጅ አማኝ ሚና ደግሞ በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ማክበር ነው (1 ቆሮንቶስ 10፡31)።

ራሳችሁን ለጋብቻ ለማዘጋጀት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ መጠራት እንደሚገባ ለመራመድ፣ እና በቃሉ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ወዳጅ ለመሆን (2 ጢሞቴዎስ 3፡16-17)፣ በነገር ሁሉ በመታዘዝ ላይ አተኩሩ። ለእግዚአብሔር በመታዘዝ መራመድን ለመማር ቀላል ዕቅድ የለም። እሱ በየዕለቱ የምናደርገው ምርጫ ነው፣ የዓለምን አተያይ ወደ ጎን በማድረግ በምትኩ እግዚአብሔርን የምንከተልበት። ለክርስቶስ እንደሚገባ መራመድ ማለት ራሳችንን በትሕትና ማስገዛት ነው፣ ለብቸኛው መንገድ፣ ለብቸኛው እውነት፣ እና ለብቸኛው ሕይወት፣ በየቀኑና በየደቂቃው አኳያ። ያ ነው እያንዳንዱ አማኝ መዘጋጀት የሚያስፈልገው፣ ጋብቻ ብለን ለምንጠራው ታላቅ ስጦታ።

በመንፈሳዊነት የበሰለና ከእግዚአብሔር ጋር የሚራመድ ሰው ከማንም ይልቅ ለጋብቻ የተዘጋጀ ነው። ጋብቻ ቁርጠኝነትን፣ ጥልቅ ስሜትን፣ ትሕትናን፣ ፍቅርን፣ እና አክብሮትን ይጠይቃል። እነዚህ ነገሮች ጽኑማስረጃ ናቸው፣ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ወዳጅነት ባለው ሰው። ራሳችሁን ለጋብቻ ስታዘጋጁ፣ እግዚአብሔር እንዲያበጃችሁ እና እንዲያስተካክላችሁ በመፍቀድ ላይ አተኩሩ፣ ለየትኛው ሰው ወይም ሴት እንድትሆኑ ለሚፈቅደው (ሮሜ 12፡1-2)። ራሳችሁን ለእርሱ ካስገዛችሁ፣ እሱ ለጋብቻ ብቁ ያደርጋችኋል፣ ያ አስደናቂ ዕለት ሲደርስ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ራሴን እንዴት ለጋብቻ ማዘጋጀት እችላለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries