settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አንድ ክርስቲያን ቤተሰብ አባካኝ ወንድ ወይንም ሴት ልጅ ቢኖረው ምን ማድረግ አለበት?

መልስ፤


በጠፋው ልጅ ታሪክ ውስጥ አማኝ የሆኑ ቤተሰቦች ለጆቻቸው ሲያሳድጉ ካሳዩአቸው የተቃረነ አካሄድ ሲሄዱባቸው ሊጠቀሙበት የሚችሉ የተለያዩ መርሆዎችን እናገኛለን፡፡ (ሉቃ 15:11-32) ወላጆ ለጆችቻቸው የጉልምስና እድሜ ከደረሱ በኋላ በቤተሰባቸው ሥልጣን ስር እንዳልሆኑ ማሰብ አለባቸው፡፡

በጣፋው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታናሹ ልጅ የውርስ ድርሻውን ወስዶ ወደ ሌላ ሃገር ሄደና አባከነው፡፡ ዳግም ባልተወለደ ልጅ ጉዳይ በቀላሉ ሊሆን የሚጠበቀው ይህ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ግልጽ በሆነ መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ይሄድ የነበረ ለጅ ‹‹የጠፋው ልጅ›› እንለዋለን፡፡ ትርጉሙም ‹‹ያለውን ሃብት ጥሪት በከንቱ ያባከነ›› ማለት ነው፡፡ ይህ ቤቱን ትቶ ሄዶ ወላጆቹ የለፉበትን መንፈሳዊ ውርስ ያባከነ ልጅ ጥሩ መግለጫ ነው፡፡ ይህ ልጅ እነዚያን በመመገብ በማስተማር ፍቅር እና እንክብካቤ ይደረጉለትን የነበረበትን አመታት በእግዚአብሔር ላይ ሲያምጽ ረሳው፡፡ ማንኛውም በእግዚአብሔር ላይ የሚደግ አመጽ በመጀመሪያ ቤተሰብንና የቤተሰብን ስልጣን በመቃረን ይገለጻል፡፡

ልብ እንበል በምሳሌው ውስጥ የምንመለከተው አባት ልጁን ከመሄድ አላስቆመውም፡፡ ወይንም ጥበቃን ሊያደርግለት ከኋላው አልተከተለውም፡፡ ይልቁንም ቤተሰቦቹ በታማኝነት በቤት ሆነው ይጸልዩለት ነበር፡፡ ለጁ ‹‹ወደ ልቡ ሲመለስ›› ዞሮ ተመልሶ ሲመጣ ቤተሰቦቹ ይጠብቁት ነበርና ለጁን ሊቀበሉት ገና ከሩቅ ሳለ ሮጠው ወጡ፡፡

ልጆቻችን በገዛ አስተሳሰባቸው ሲሄዱ ይህን እናስብ ይህ ለማድረግ እድሜያቸው እስከደረሰ፤ የሚመርጡት ምርጫ ምን አይነት ችግር ሊያመጣባቸው እንደሚችል እያወቅን፤ ወላጆች ልንለቃቸው እንዲሄዱ ልንተዋቸው ያስፈልጋል፡፡ ቤተሰው ሊከተላቸው አያስፈልግም እንዲሆም ተከትሎ በሚመጣው ወጤት ጣልቃም አይገቡም፡፡ ይልቁንም ቤተሰብ በታማኝነት እየጸለዩ ንስሐና አቅጣጫ የመለውጥ ምልክቶችን እስኪያዩባቸው እቤት ሆነው መቆየት አለባቸው፡፡ ይህ እስኪሆን ቤተሰብ ምክራቸውን ይቀጥሉ አመጻቸውን አይተባበሩ እና ጣልቃም አይግቡ (1 ጴጥ 4:15) ፡፡

አንድ ጊዜ ልጆች ህግ የሚፈቅድላቸው እድሜ ለይ ከደረሱ ተጠያቂነታቸው ለእግዚአብሔርና መንግስት ስልጣን ለሰጠው አካል ነው (ሮሜ 13:1-7)፡፡ እንዱሆም እነርሱ አንድ ጊዜ ከእግዚአብሄር አቅጣጫ የራሳቸውን እርምጃ ከወስዱ ወደ ጌታ ልንቀርብና በጌታ ፊት ልንቆም የጠፉ ልጆቻችንን እንደቤተሰብ በፍቅርና በጸሎት ልንረዳቸው እንችላለን፡ እግዚአብሔረ ብዙ ጊዜ በራሳችን የምናመጣውን ችግር ስቃይ እኛን ወደ ጥበብ ስለሚጠቀምበት እያንዳንዱ ግለሰብ በትክክል በራሱ ምላሽ መስጠት አለበት፡፡ እግዚአብሔር እንጂ እኛ እንደቤተሰብ ልናድናቸው አንችልም፡፡ ጌዜው እስኪደርስ ድረስ ልንጠባበቅ ልንጸልይ ነገሩን በእግዚአብሔር እጅ ላይ ልንተው ያስፈልጋል፡፡ ይህ እጅግ የሚያሳምም ሂደት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ቃል ስናደርግ በአዕመሮና በልባችን ሰላም ይሰጠናል፡፡ በልጆቻችን ልንፈርድ አንችልም ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ በዚህ ትልቅ መጽናናት እረፍት ይሆንልና፡፡ ‹‹የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን? ››(ዘፍ 18:25፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አንድ ክርስቲያን ቤተሰብ አባካኝ ወንድ ወይንም ሴት ልጅ ቢኖረው ምን ማድረግ አለበት?
© Copyright Got Questions Ministries