ጥያቄ፤
ክርስቲያኖች ስለ ሳይኪክ የሚኖራቸው አመለካከት ምንድን ነው?
መልስ፤
መጽሐፍ ቅዱስ በአጽንኦት መናፍስት ጠሪነትነ፤ (occult) ይቃወማል (ዘሌ 20:27; ዘዳ 18:10-13). ሆርስኮፕ የካርታ ጫወታ አስትሮሎጂ ጠንቋዩች የመዳፍ ንባብ እንዚህም በዚህ ምድብ የሚመደቡ ናቸው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦች የሚመሰረቱት አማልክቶች መናፍስት ወይንም የሚወዱአቸው የሞቱባቸው ምክርና አቅጣጫ ይሰጡናል ከሚል ነው፡፡ ‹‹አማልክቶች›› ‹‹መናፍስት›› አጋንንቶች ናቸው (2 ቆሮ 11:14-15)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ስለማመን ምንም ፍንጭ በሞት የተለዩን ሰዎች ሊገናኙን እንደሚችሉ አይሰጠንም፡፡ አማኞች ቢሆኑ በሰማይ በጣም በተሻለ ስፍራ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረትን እያደረጉ ነው፡፡ አማኞች ካልነበሩ በማያቋርጥ አሳት እግዚአብሔርን በመቃወማቸው እና በእርሱ ላይ በማመጻቻ እየተቀጡ ነው፡፡
ስለዚህ የሚወዱን ሰዎች እኛን የማይገናኙን ከሆነ ሙታንን የሚያናግሩ ማናፍስት ጠሪዎች ከተፈጥሮ ውቺ የሆነ ነገር የሚያደረጉ ሳይኪኮች ከየት መረጃዎችን ሊያገኙ ይችላሉ? ሳይኪኮች እንደ አጭበርባሪነታቸው ብዙ የተለያየ መንገድ አላቸው፡፡ ሳይኪኮች ብዙ መረጃዎች ከተራ ሰዎች ያገኛሉ ይህም የተረጋገጠ ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በስልክ የግለሰቡን ማንነት በማጣራት እና ከኢንተርኔት በመፈለግ ሳይኪኮች ስሞችን የመኖሪያ አድራሻን የትውልድ ቀን የጋብቻ ቅን የቤተሰብ አባላትን …ወዘተ፡፡ ሆኖም ሳይኪኮች እነርሱ ሊያውቁት ይችላል ተብሎ የማይገመት ነገር እንደሚያውቁ የማይካድ ነው፡፡ ይህንን ከየት ነው የሚያገኙት ; መልሱ ከሰይጣን ከአጋንንት ነው፡፡ ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።
እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።›› (2 ቆሮ 11:14-15). ሥራ 16:16-18 በነገ ውስጥ ያለውን የሚናገረውን መንፈስ ከእርሷ ጳውሎስ ገስጾ እስከሚያስውጣውድረስ እንመለከታለን፡፡
ሰይጣን የሚረዳን ሊያስመስል ይችላል፡፡ መልካም መስሎ ሊታይ ይችላል፡፡ ሰይጣን እና አጋንንቶቹ የሳይኪክ መረጃን ስለ አንድ ሰው እግዚአብሔር ወደ ከለከለው በመንፈስ ጠሪነት ውስጥ አስኪከር ድረስ ይነግሩታል፡፡ በመጀሪያ ምንም የሌለበት መስሎ ይቀርባል ግን ወዲያው ሰዎች ባሳይኪክ ተጠምዶ ሳያውቁት ሰይጣን ህይወታቸውን ተቆጣጥሮ ያጠፋቸዋል፡፡ ጴጥሮስ ሲናገር ‹‹ በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ ››(1ጴጥ 5፡8)፡፡ በአንዳነድ ምክንያቶች እራሳቸው ሳይኪኮች ይታለላሉ የተቀበለቱን መረጃ ትክክለኛ ምንጭ አያውቁትም፡፡ ጉዳዩ ምንም ይሁን መረጃው ከየትም ይምጣ መንፈስ ጠሪነት ጥንቆላ ኮከብ ቆጠራ የእግዚአብሔር በሆነው መንገድ መረጃን ማግኘት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም፡፡ እግዚአብሔር እንዴት ነው ፈቃዱን በህይወታችን እንድናስተውል የሚፈልገው; የእግዚአብሔር ፈቃድ ግልጽ ቀላል ነው ግን ኃይለኛና ውጤታማ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እናጥና (2ኛ ጢሞ 3፡16-17) ጥበብንም እንዲሰጠን እንለምን(ያዕ 1፡5)፡፡
English
ክርስቲያኖች ስለ ሳይኪክ የሚኖራቸው አመለካከት ምንድን ነው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?