settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የቤተ-ክርስቲያን ዓላማ ምንድነው?

መልስ፤


ሐዋርያት ሥራ 2፡42 የቤተ-ክርስቲያን ዓላማ የሆነ መግለጫ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። “በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።” በዚህ ቁጥር መሠረት፣ የቤተ-ክርስቲያን ዓላማ/ተግባር መሆን ያለበት 1) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዶክትሪንን ማስተማር፣ 2) ለአማኞች ኅብረት ስፍራ በስጠት፣ 3) የጌታን ራት ማዘጋጀት፣ እና 4) መጸለይ ነው።

ቤተ-ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዶክትሪንን ስታስተምረን በእምነታችን ሥር እየሰደድን እንሄዳለን። ኤፌሶን 4፡14 ይነግረናል። “እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም።” ቤተ-ክርስቲያን የአንድነት ስፍራ መሆን አለባት፣ እዚያም ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው የሚሰጣጡበት እና እርስ በርሳቸው የሚከባበሩበት (ሮሜ 12፡10)፣ እርስ በርሳቸው የሚገሠጹበት (ሮሜ 15፡14)፣ እርስ በርሳቸው ደግነትንና ርኅራኄን የሚያሳዩበት (ኤፌሶን 4፡32)፣ እርስ በርስ የሚበረታቱበት (1 ተሰሎንቄ 5፡11)፣ እንዲሁም እጅግ በሚጠቅመው እርስ በርስ እንዲፋቀሩ ነው (1 ዮሐንስ 3፡11)።

ቤተ-ክርስቲያን አማኞች የጌታን ራት የሚካፈሉባት ስፍራ መሆን ይኖርባታል፣ በእኛ ምትክ ክርስቶስ ደሙን ማፍሰሱንና መሞቱን ለማስታወስ (1 ቆሮንቶስ 11:23-26)። “እንጀራን የመቁረስ” ጽንሰ-ሐሳብ (ሐዋርያት ሥራ 2፡42) አብሮ የመመገብንም ሐሳብ ይዟል። ይህም አንደኛው ምሳሌ ነው፣ ቤተ-ክርስቲያን ኅብረትን የምታሳድግበት። የመጨረሻው የቤተ-ክርስቲያን ዓላማ፣ እንደ ሐዋርያት ሥራ 2፡42 መጸለይ ነው። ቤተ-ክርስቲያን ጸሎትን፣ ጸሎት ማስተማርን፣ እና ተግባራዊ ጸሎት ማድረግን የምታስፋፋ ስፍራ ነች። ፊሊጵስዩስ 4፡6-7 ያበረታታናል፣ “ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።”

ሌላው ለቤተ-ክርስቲያን የተሰጣት ተልዕኮ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያለውን የመዳንን ወንጌል ማወጅ ነው (ማቴዎስ 28:18-20፤ ሐዋርያት ሥራ 1:8)። ቤተ-ክርስቲያን የተጠራችው ታማኝ ሆና ወንጌልን በቃልም ሆነ በተግባር እንድታካፍል ነው ቤተ-ክርስቲያን ለማኅበረሰቡ “የብርሃን ቤት” መሆን ይኖርባታል፣ ሰዎችን ወደ ጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማመልከት። ቤተ-ክርስቲያን ወንጌልን ማሰራጨት ይኖርባታል እንዲሁም አባሎቿም ወንጌልን እንዲያውጁ ማዘጋጀት ይኖርባታል (1ጴጥሮስ 3፡15)።

ጥቂት የማጠቃለያ የቤተ-ክርስቲያን ዓላማዎች በያዕቆብ 1፡27 ተሰጥተዋል፡ ”ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።” ቤተ-ክርስቲያን በችግር ላይ ያሉትን በመርዳት አገልግሎት መሳተፍ ይኖርባታል። ይህም ወንጌልን ማካፈል ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ለሰውነት የሚያስፈልጉትን መስጠት ይኖርባታል (ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያ) እንደ አስፈላጊነቱና እንደተመቸ። ቤተ-ክርስቲያን አማኞችን በክርስቶስ ማብቃት ደግሞ ይጠበቅባታል፣ ኃጢአትን ድል በሚያደርጉበት ትጥቅ፣ እናም ከዓለም እድፍ ነጻ ሆነው እንዲጠበቁ። ይህ የሚደረገው በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና በክርስቲያን ኅብረት ነው።

ስለዚህ፣ የቤተ-ክርስቲያን ዓላማ ምንድነው? ጳውሎስ ለቆሮንቶስ አማኞች ግሩም ማሳያ ሰጥቷል። ቤተ-ክርስቲያን የእግዚአብሔር እጅ፣ አፍ፣ እና እግር ነች፣ በዚህ ዓለም—የክርስቶስ አካል (1 ቆሮንቶስ 12:12-27)። እኛ ማድረግ ይጠበቅብናል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በዚህ ምድር ላይ ቢሆን ኖሮ ያደርግ የነበረውን። ቤተ-ክርስቲያን “ክርስቲያን፣” “ክርስቶስን-መሰል” እና ክርስቶስን የምትከተል መሆን ይኖርባታል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የቤተ-ክርስቲያን ዓላማ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries