settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዘረኝነት፣ ፍርደ-ገምድልነት፣ እና አድሏዊነት ምን ይላል?

መልስ፤


በዚህ ውይይት ላይ መረዳት የሚገባው ቀዳሚ ነገር አንድ ብቸኛ ዘር መኖሩን ነው—የሰው ዘር። ካውካሲያኖች፣ አፍሪካውያን፣ እስያውያን፣ ህንዶች፣ ዓረቦች፣ እና አይሁድ የተለያዩ ዘሮች አይደሉም። ይልቁን፣ እነሱ የሰው ዘር የተለያዩ ዝርያዎች ናቸው። ሁሉም የሰው ልጆች ተመሳሳይ አካላዊ ባሕርይ አላቸው (በርግጥ፣ በተወሰኑ ልዩነቶች)። በዋነኛነትም፣ ሁሉም የሰው ልጆች በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል ነው የተፈጠሩት (ዘፍጥረት 1፡26-27)። እግዚአብሔር ዓለምን እጅግ ወድዷል፣ ኢየሱስን ልኮ ሕይወቱን ለእኛ ያኖር ዘንድ (ዮሐንስ 3፡16)። “ዓለም” በግልጽ የሁሉንም ዘር ወገኖች ያካትታል።

እግዚአብሔር አድሏዊነት ወይም የተለየ ውዴታ አያሳይም (ዘዳግም 10፡17፤ ሐዋ. 10፡34፤ ሮሜ 2፡11፤ ኤፌሶን 6፡9)፣ እኛም እንደዚያው። ያዕቆብ 2፡4 አድሏዊነት የሚያደርጉትን የሚገልጸው “ክፉ ሐሳብ ያላቸው ዳኞች” በሚል ነው። ይልቁንም እኛ ባልንጀሮቻችንን እንደራሳችን መውደድ ይኖርብናል (ያዕቆብ 2፡8)። በብሉይ ኪዳን፣ የሰው ልጆችን በሁለት “የዘር” ቡድኖች መድቧል፡ አይሁድና አሕዛብ። እግዚአብሔር ለአይሁድ የነበረው ሐሳብ የካህናት መንግሥት እንዲሆኑ ነበር፣ የአሕዛብን ሕዝቦች እንዲያገለግሉ። ባንጻሩ፣ ባብዛኛው ክፍል፣ አይሁድ በማዕርጋቸው ተኩራርተው አሕዛብን ናቁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ወደ ፍጻሜ አመጣው፣ የጠብን ግድግዳ በማፍረስ (ኤፌሶን 2፡14)። ማንኛውም ዓይነት ዘረኝነት፣ ፍርደ-ገምድልነት፣ አድሏዊነት፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ለሠራው ሥራ ተጻራሪ ነው።

ኢየሱስ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ አዞናል፣ እሱ እንደሚወደን (ዮሐንስ 13፡34)። እግዚአብሔር አድሏዊ ካልሆነና እኛንም ያለ አድልዖ ከወደደን፣ እንግዲያውስ እኛም ሌሎችን በተመሳሳይ የላቀ ደረጃ ልንወድ ይገባል። ኢየሱስ፣ ማቴዎስ 25 ላይ ሲያስተምር ለማንኛውም ላነሱት ወንድሞቹ ያደረግነው፣ ለእሱ አድርገነዋል። ሰውን በማንቋሸሽ ከያዝነው፣ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረን ሰው አላግባብ ያዝነው ማለት ነው፤ እግዚአብሔር የወደደውን አንዱን ጎድተነዋል፣ እሱም ክርስቶስ የሞተለትን።

ዘረኝነት በተለያየ መልኩ እና በተለያየ ደረጃዎች፣ ለሰው ልጆች መቅሠፍት ሆኗል፣ ለሺህ ዓመታት። ወንድሞችና እኅቶች የሁሉም ዘሮች፣ ይህ መሆን የለበትም። የዘረኝነት፣ የፍርደ-ገምድልነት፣ እና የመድልዖ ሰለባዎች ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው። ኤፌሶን 4፡32 እንደሚያውጀው፣ “እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ሩኅሩኆች ሁኑ፣ እርስ በርሳችሁ ይቅር በመባባል፣ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ።” ዘረኞች የእናንተ ይቅርታ አይገባቸው ይሆናል፣ እኛ ግን የእግዚአብሔር ይቅርታ ይገባናል። ዘረኝነትን፣ ፍርደ-ገምድልነትን፣ እና አድሏዊነትን የሚለማመዱ ንስሐ መግባት ይኖርባቸዋል። “ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ” (ሮሜ 6፡13)። ገላትያ 3፡28 አጠቃሎ ያስቀምጠዋል፣ “አይሁድም ቢሆን የግሪክ ሰው የለም፣ ባሪያም ቢሆን ጨዋ፣ ወንድ ሆነ ሴት፣ እናንተ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ናችሁና።”

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዘረኝነት፣ ፍርደ-ገምድልነት፣ እና አድሏዊነት ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries