ጥያቄ፤
የክርስቲያን እርቅ ምንድነው? ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ለምን ያስፈልገናል?
መልስ፤
እርቅ ማለት ከአለመግባባት በኋላ ኅብራዊ አቋም ያለው የግንኙነት መመለስ ማለት ነው፤ እሱም ከአለመግባባት ወደ መግባባት የሚያመጣ ነው፣ በሁለት ወገኖች መካከል። የክርስቲያን እርቅ የእግዚአብሔር ሥራ ነው፣ በክርስቶስ በኩል፣ ይኸውም እሱ የሰውን ልጅ ከእሱ ጋር ያለውን ግንኙነት አመቺ ወደ ሆነ ሁኔታ የመለሰበት ነው።
የክርስቲያን እርቅ ቀደም ሲል ወዳጆች የነበሩና አሁን ግን ጠበኛ በሆኑ ሁለት ሰዎች ይመሰላል። ቀደም ሲል የነበራቸው መልካም አስደሳች ግንኙነት በውጥረት ወደ ተሞላ የመለያያ ነጥብ ደርሷል። እነርሱም እርስ በርስ መነጋገርን አቁመዋል፣ ብሎም ሁለቱም ቀስ በቀስ ባዕድ ሆነዋል። እነርሱም ምናልባት እርስ በርሳቸው ንቁ ባላንጦች ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ አንድ ቀን አንድ ነገር ሆነ። ሁለቱ ጠበኛ ጓደኛሞች መነጋገር ጀመሩ፤ ኩራትና ጥልቅ ምሬት ወደ ጎን ተደረጉ፤ ይቅር መባባል ተስፋፋ ተቀባይነትም አገኘ፤ መተማመን ዳግም አንሰራራ። በመጨረሻም ሰላም በሚመለስበት ጊዜ እና ወዳጆቹ ሲተቃቀፉ፣ እርቅን ተቀዳጅተዋል። እንግዲህ፣ ገምቱ፣ ከሁለቱ ወዳጆች መካከል አንደኛው ብቻ ነው ጥፋተኛው። እናም ሌለኛው ጓደኛ፣ ፍጹም ንጹሕ የሆነው ነው የእርቁን ሂደት የጀመረው - የክርስቲያን እርቅም ይሄንን ነው የሚመስለው፣ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የቀረበበት።
እርቅ በመሠረቱ ለውጥን ያካትታል። በክርስቲያን እርቅ፣ እግዚአብሔር አልተለወጠም። እሱ ፍጹም እንደሆነ ቀርቷል። እርሱ ግን እኛን ለውጦናል። በውጤቱም፣ ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ተቀየረ።
እግዚአብሔር እኛን ከእርሱ ጋር ለማስታረቅ የተጠቀመበት አገባብ የገዛ ልጁ ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ “ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ” (2 ቆሮንቶስ 5፡18-19)። በርግጥ፣ “ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን” (ሮሜ 5፡10)። የኢየሱስ ሞት ልዩነቱን ሁሉ አደረገ። ክርስቶስ ሲሞት፣ እርሱም “በመስቀሉ ደም ሰላም አደረገ” (ቆላስይስ 1፡20)።
እርቅ የሚያስፈልገን ሐቅ ማለት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረን ግንኙነት በመሰበሩ ነው። እናም እግዚአብሔር ቅዱስ ነው የሚለው ሐቅም፣ ተወቃሾቹ እኛ ነን ማለት ነው። ኃጢአታችን ከእርሱ ለይቶናል። የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሞት ይቅር የመባላችንና የጽድቃችን መሠረት ነው። በልጁ በማመን በሚሆን ጸጋ፣ እግዚአብሔር ወደ ክርስቶስ አምሳል ዳግም ፈጽሞ አበጀን። እግዚአብሔርና ሰው ወደ አንድነት መጡ፡ የቀድሞዎቹ በኃጢአት የሞቱት ወደ አዲስ ሕይወት ተነሥተዋል። “ከእንግዲህስ ጠላቶች፣ ክፉዎች፣ ኃጢአተኞች፣ ወይም አቅመ-ቢሶች አይደለንም፣ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም (ሮሜ 5፡5)። እሱም የሕይወታችንን አቋም ሙሉ ለሙሉ የቀየረ ነው።”
(“እርቅ፣” ውድረፍ፣ ደብልዩ.፣ ቤከር የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ መለኮት ወንጌላዊ መዝገበ ቃላት፣ ኤልዌል፣ ደብልዩ.፣ ኤዲተር፣ ቤከር መጻሕፍት፣ 1996)።
ሊባል የሚችለው፣ ሞላው መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቲያን እርቅ ታሪክ ነው። የእግዚአብሔር ወዳጅነታችን ተለይቶ የጀመረው ስፍራ በዔድን ገነት ነው፣ የማይተፋፈር እና ሕያው የሆነ ኅብረት ከእግዚአብሔርና እርስ በርሳችን ነበረን። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፣ እናም ግንኙነታችን ሁሉ ተሰበረ። እኛም የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆንን፣ የገዛ ራሳችንን መንገዶች የምንፈልግ እና ግልጽ በሆነ ጠበኝነት ከእርሱ ጋር የምንኖር። ሙሉው ቅዱስ ቃል፣ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ከራሱ ጋር እንዲያስታርቀን የተጻፈ ነው። እኛ ልንኮበልል እንችላለን፣ እሱም ይከታተለናል። እኛ እንደ በጎች ተበታትነናል፣ እሱም መልካሙን እረኛ ላከልን። እኛ በጨለማ ተደበቅን፣ እሱም እውነተኛውን ብርሃን ላከልን። እኛ የሞትነው ራሳችን በፈጠርነው ድርቅ ነው፣ እሱም የሕይወትን ውኃ ላከልን።
የእግዚአብሔር ጸጋ እና ደግነት በክርስቲያን እርቅ በሙላት እየታየ ነው። “እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ። (ቆላስይስ 1:21–22)።
ከእግዚአብሔር ጋር እንደታረቁ ሁሉ፣ “የማስታረቅ አገልግሎት” ተሰጥቶናል (2 ቆሮንቶስ 5፡18)። “የማስታረቅ ቃል” (ቁጥር 19) በአመኔታ አኖረ። እኛም አሁን ወንጌልን እየሞተ ላለው ዓለም እንወስዳለን፣ “እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” (ቁጥር 20)። የኢየሱስ የመስቀል ፍጹም መሥዋዕት የኃጢአት ማስተሠርያ ሆኗል (ዕብራውያን 2፡17)። በሞቱ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ኅብረት ስምም እንዲሆን አደረገ። እኛም ያላመኑትን እንማልዳለን፣ በክርስቶስ ያምኑ ዘንድና የክርስቲያን እርቅን ደስታዎች እንዲያውቁ።
English
የክርስቲያን እርቅ ምንድነው? ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ለምን ያስፈልገናል?