ጥያቄ፤
የክርስቲያን መቤዠት ምን ማለት ነው?
መልስ፤
እያንዳንዱ ሰው መቤዠት ያስፈልገዋል። የእኛ ተፈጥሯዊ ሁኔታ የኃጢአት ባሕርይ አለው፡ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል” (ሮሜ 3፡23)። የክርስቶስ ቤዛነት ከኃጢአት ነጻ አውጥቶናል፣ “በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ” እንደተባለ (ሮሜ 3፡24)።
የመቤዠት ጠቀሜታ የዘላለም ሕይወትን ያካትታል (ራዕይ 5፡9-10)፣ የኃጢአት ይቅርታ (ኤፌሶን 1፡7)፣ ጽድቅ (ሮሜ 5፡17)፣ ከርግማን ሕግ (ገላትያ 3፡13)፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል መሆን (ገላትያ 4፡5)፣ ከኃጢአት ባርነት ነጻ መውጣት (ቲቶ 2:14፤ 1 ጴጥሮስ 1:14-18)፣ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም (ቆላስይስ 1፡18-20)፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ማደር (1 ቆሮንቶስ 6፡19-20)። የተቤዡ መሆን፣ እንግዲያውስ፣ ይቅር መባል ነው፣ ቅዱስ፣ መጽደቅ፣ ነጻ መሆን፣ ልጅነት፣ እና መታረቅ ነው። ደግሞም መዝሙር 130፡7-8፤ ሉቃስ 2፡38፤ እና ሐዋ. 20፡28 ተመልከት።
መቤዠት የሚለው ቃል “መግዛት” ማለት ነው። ቃሉ በተለይ ጥቅም ላይ የሚውለው፣ ባርያን ነጻ ለማውጣት መግዛትን ለመጥቀስ ነው። የዚህ ቃል አተገባበር ለክርስቶስ የመስቀል ሞት ጋር እጅጉን ያሳምናል። እኛ “የተዋጀን” ከሆንን፣ እንግዲያውስ የእኛ ቀዳሚ ሁኔታ ባርነት ነበር። እግዚአብሔር ነጻነታችንን ገዝቷል፣ እናም እኛ ከአሁን በኋላ በኃጢአት ባርነት አይደለንም ወይም ለብሉይ ኪዳን ሕግ። ይህ ዘይቤአዊ “የመዋጀት” አጠቃቀም የገላትያ 3፡3 እና 4፡5 ትምህርት ነው።
ከክርስቲያን የመዋጀት ጽንሰ-ሐሳብ ጋር በተያያዘ ያለው ቃል ዋጆ/መቤዣ ነው። ኢየሱስ ለእኛ ከኃጢአት መፈታትና ለቅጣቱ ዋጋ ከፍሏል (ማቴዎስ 20፡28፤ 1ጢሞቴዎስ 2፡6)። የእሱ ሞት ለእኛ ሕይወት ቅያሪ ነው። በርግጥ፣ ቅዱስ ቃሉ ፍጹም ግልጽ ነው፣ ማለትም መቤዠት የሚቻለው “በደሙ” ነው፣ በሞቱ (ቆላስይስ 1፡14)።
የመንግሥተ ሰማያት አደባባዮች የሚሞሉት በቀድሞዎቹ ምርኮኖች ነው፣ በገዛ ራሳቸው ሥራ ሳይሆን፣ ራሳቸውን የተዋጁ፣ ይቅር የተባሉ፣ እና ነጻ ሆነው በሚያገኙ። የኃጢአት ባሪያዎች ቅዱሳን ሆነዋል። አዲስ ዝማሬ ብንዘምር የሚያስገርም አይሆንም - የውዳሴ መዝሙር፣ ለታረደውና ለተዋጀን (ራዕይ 5፡9)። እኛ የኃጠአት ባሪያዎች ነበርን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ለመለያየት የተኮነንን። ኢየሱስ ዋጋውን ከፈለ እኛን ለመዋጀት፣ በውጤቱም ከባርነት ነጻ አወጣን፣ እናም ከዛ ኃጢአት ዘላለማዊ ውጤት አዳነን።
English
የክርስቲያን መቤዠት ምን ማለት ነው?