settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ንስሐ ምንድነው እሱስ ለድኅነት ያስፈልጋልን?

መልስ፤


ብዙዎች ንስሐ የሚለውን ቃል የሚረዱት “ከኃጢአት መመለስ” በሚል ነው። ኃጢአትን መጸጸት እና ከእሱ መመለስ ከንስሐ ጋር ይያያዛል፣ ነገር ግን እሱ ተለይቶ ግልጽ የሆነው የቃሉ ፍቺ አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ፣ ንስሐ መግባት የሚለው ቃል ፍችው “የአንዱ አስተሳሰብ ሲለወጥ” ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ እንደሚነግረን እውነተኛ ንስሐ የሥራ ለውጥን ያስከትላል (ሉቃስ 3:8–14፤ ሐዋ.3:19)። አገልግሎቱን ሲያጠቃልል ጳውሎስ እንዳወጀው፣ “ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሐ ይገቡ ዘንድና ለንስሐ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ዘወር ይሉ ዘንድ ተናገርሁ” (ሐዋ. 26፡20)። የተሟላው የመጽሐፍ ቅዱስ የንስሐ ፍቺ ያስተሳሰብ ለውጥ ነው፣ እሱም የሥራ ለውጥን የሚያስከትል።

እንግዲያውስ፣ በንስሐ እና በድኅነት/መዳን መካከል ያለው ግንኙነት ምንድነው? የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በተለይ ድኅነትን በተመለከተ በንስሐ ላይ ያተኩራል (ሐዋ. 2:38፤ 3:19፤ 11:18፤ 17:30፤ 20:21፤ 26:20)። ንስሐ መግባት፣ ከደኅንነት ጋር በተያያዘ፣ አስተሳሰብህን መቀየር ማለት ነው፣ ኃጢአት እና ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከተ። በበዓለ ኀምሳ ቀን ጴጥሮስ በስብከቱ (ሐዋ. ምዕራፍ 2) ላይ እሱ ያጠቃለለው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ለሕዝቡ ጥሪ በማቅረብ ነው (ሐዋ. 2፡38)። ከምንድነው ንስሐው? ጴጥሮስ ኢየሱስን ላልተቀበሉት ሰዎች ጥሪ ያቀርባል (ሐዋ. 2፡36) ስለዛ ኃጢአት አስተሳሰባቸውን እንዲቀይሩ እና ስለ ክርስቶስ ስለ ራሱ ያላቸውን አስተሳሰብ እንዲቀይሩ፣ እሱ በርግጥ “ጌታና ክርስቶስ” ስለ መሆኑ እውቅና እንዲሰጡ (ሐዋ. 2፡36)። ጴጥሮስ ለሕዝቡ ጥሪ ያቀርባል አስተሳሰባቸውን እንዲቀይሩ፣ ያለፈውን ክርስቶስን ያለመቀበላቸውን እንዲጸየፉ፣ እናም በእሱ ላይ እምነት እንዲይዙ፣ እንደ ሁለቱም፣ እንደ መሲሕ እና አዳኝ።

ንስሐ ባለፉት ጊዜያት በተሳሳተ አስተሳሰብ ውስጥ እንደሆኑ መገንዘብን ሲያካትት፣ ለወደፊቱ ደግሞ በትክክል ለማሰብ ቁርጠኝነትን ይይዛል። ንስሐ የገባ ሰው ቀድሞ ለተያዘበት የልቦና ውቅር “ዳግመኛ የማሰብ” አገባብ አለው። የዝንባሌ ለውጥ ይኖራል፣ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ኃጢአት፣ ስለ ቅድስና፣ እና የእግዚአብሔርን ፍቃድ ስለ ማድረግ አዲስ ያስተሳሰብ መንገድ። እውነተኛ ንስሐ “በጎ በሆነ ኀዘን” ይደገፋል፣ እሱም “ወደ ደኅንነት ያመራል” (2 ቆሮንቶስ 7፡10)።

ንስሐ እና እምነትን እንደ አንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ አድርጎ መውሰድ ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን ለመጣል አይቻልም፣ በቅድሚያ ስለ ኃጢአታችሁ፣ እና ስለ ኢየሱስ ማንነትና እሱም ስላደረገው ሥራ አስተሳሰባችሁ ሳይቀየር። ሆን ተብሎ ከተደረገ አለመቀበል የሆነ ንስሐ ቢሆን፣ ወይም ከአላዋቂነት፣ ወይም ከፍላጎት ያለመኖር የሆነ ንስሐ ቢሆን የአስተሳሰብ ለውጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንስሐ፣ ከደኅንነት ጋር በተያያዘ፣ ክርስቶስን ካለመቀበል የአስተሳሰብ ለውጥ በክርስቶስ ወደ ማመን መምጣት ነው።

ንስሐ፣ ድኅነትን/መዳንን ለማግኘት የምንሠራው ሥራ አይደለም። ማንም ቢሆን ንስሐ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር ሊመጣ አይችልም፣ እግዚአብሔር ያንን ሰው ወደ ራሱ እስካልሳበው ድረስ (ዮሐንስ 6፡44)። ንስሐ እግዚአብሔር የሚሰጠው ነገር ነው – እሱ ሊሆን የሚችለው በእርሱ ጸጋ ብቻ ነው (ሐዋ. 5:31፤ 11:18)። ማንም ንስሐ ሊገባ አይችልም፣ እግዚአብሔር ንስሐ እስካልሰጠው ድረስ። መዳን ሁሉ፣ ንስሐ እና እምነትን ጨምሮ፣ እግዚአብሔር እኛን ወደ ራሱ የመሳቡ ውጤት ነው፣ ዓይናችንን የመክፈቱ፣ ልባችንን መቀየሩ። የእግዚአብሔር ትዕግሥት ወደ ንስሐ መራን (2 ጴጥሮስ 3፡9)፣ ቸርነቱ እንዳደረገው (ሮሜ 2፡4)።

ንስሐ ደኅንነትን የሚያስገኝ ሥራ ባይሆንም፣ ንስሐ ወደ ደኅንነት በሥራ ውጤት ያመጣል። በርግጠኝነት አስተሳሰብን መቀየር አይቻልም፣ የድርጊት ለውጥን ለማምጣት ምክንያት እስካልሆነ ድረስ። በመጽሐፍ ቅዱስ፣ ንስሐ የባሕርይ ለውጥን በውጤት ያመጣል። በዚህ ምክንያት ነው፣ መጥምቁ ዮሐንስ “ለንስሐ ፍሬ እንዲያፈሩ” ለሕዝቡ ጥሪ ያቀረበው (ማቴዎስ 3፡8)። በእውነት ከኃጢአቱ ንስሐ የገባና በክርስቶስ ያለውን እምነት ተግባራዊ የሚያደርግ ሰው፣ ለተለወጠ ሕይወት ማስረጃ የሚሰጥ ነው (2 ቆሮንቶስ 5፡17፤ ገላትያ 5፡19-23፤ ያዕቆብ 2፡14-26)።

ንስሐ በተጨባጩ ሕይወት ምን እንደሚመስል ለመመልከት፣ ማድረግ ያለብን ነገር ወደ ዘኪዮስ ታሪክ መመለስ ነው። እሱ የሚያጭበረብርና የሚሰርቅ ሰው ነበር፣ ብሎም የተቀማጠለ ሕይወትን የሚኖር፣ በግፍ ባገኘው ገንዘብ - ኢየሱስን እስኪያገኝ ድረስ። በዛች ነጥብ እሱ ሥር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ አደረገ፡ “ተመልከት፣ ጌታ ሆይ!” አለ ዘኬዎስ። “ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ” (ሉቃስ 19፡8)። ኢየሱስ በደስታ አውጇል፣ መዳን ወደ ዘኪዎስ ቤት ስለ መምጣቱ፣ እናም ቀረጥ ሰብሳቢው እንኳ አሁን “የአብርሃም ልጅ” ሆኗል (ቁጥር 9) - ለዘኪዎስ እምነት ማጣቀሻ። አጭበርባሪው ለጋስ ሆነ፤ ሌባው ካሳ ከፋይ ሆነ። ንስሐ ማለት ይሄ ነው፣ ከክርስቶስ ጋር በእምነት መወዳጀት።

ንስሐ ባግባቡ ሲገለጽ፣ ለደኅንነት አስፈላጊ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንስሐ ስለ ኃጢአትህ ያለህን አስተሳሰብ መቀየር ማለት ነው ― ኃጢአት ከእንግዲህ በኋላ የምትጫወትበት አሻንጉሊት አይደለም፤ እሱ ወዲያ የምንተወው ዓይነት ነገር ነው፣ “ከሚመጣው ቁጣ እንደምንርቅ” (ማቴዎስ 3፡7)። እሱ ደግሞ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን አስተሳሰብ መቀየር ነው ― ከእንግዲህ በኋላ አይዘበትበትም፣ ችላ አይባልም፣ ወይም አይተውም፤ እሱ በጥብቅ የምንይዘው አዳኝ ነው፤ እሱ ሊሰገድለት እና ሊመለክ የሚገባው ጌታ ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ንስሐ ምንድነው እሱስ ለድኅነት ያስፈልጋልን?
© Copyright Got Questions Ministries