settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ለኔ የሚሆን ትክክለኛው ሐይማኖት የትኛው ነው?

መልስ፤


ቀልጣፋ ሬስቶራንቶች በቀላሉ የሚስቡን የፈለግነውን ምግብ በምንወደው መንገድ እንድናዝ መንገድ ስለሚከፍቱልን ነው። ጥቂት ካፌዎች ደግሞ ከመቶ በላይ የተለያዩ የቡና ጣዕም እንደሚያቀርቡ በጉራ ይናገራሉ። መኖሪያ ቤቶችና መኪናዎችን ስንገዛ እንኳ የምንፈልገው ምርጫ እንዲያሟላ እንሻለን። በቼኮላት፣ በቫኒላና በእንጆሪ ዓለም ታጥረን መኖር አንፈልግም። ፍላጎት ንጉስ ነው! እንደግላዊ ፍላጎትህና ምርጫህ የምታገኝበት ሁሉ የተሟላበት ዘመን ነው።

ለአንተ ብቻ ትክክለኛ ሐይማኖት የማግኘቱ ሁኔታስ ምን ይመስላል? ወቀሳ አልባ፣ ብዙ ጫና የሌለውና ይህንን አድርግ አታድርግ እያለ የማያስቸግር ሐይማኖት ብታገኝስ? ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ያውና እዚያ አለ ነገር ግን ሐይማኖት እንደሚወዱት አይስክሬም የሚመረጥ ነው እንዴ?

ትኩረታችንን ለመሳብ የሚሻሙ በርካታ ድምፆች ስላሉ ለምን ብሎ ነው አንድ ሰው ኢየሱስን ከሌሎች ማለትም ከመሐመድ ወይም ከኮንፊሸየስ፣ ከቡድሐ ወይም ቻርለስ ቴዝ ራስል ወይም ከጆሴፍ እስሚዝ አስበልጦ የሚመርጠው? ዞሮዞሮ ሁሉም መንገዶች የሚያደርሱት ወደ መንግስተ ሰማይ አይደለም እንዴ? በመሰረቱ ሁሉም ሐይማኖቶች አንድ አይደሉም እንዴ? እንደ እውነቱ ከሆነ ሁሉም ሐይማኖቶች ወደ መንግስተ ሰማይ አያመሩም። ሁሉም መንገዶች ወደ ኢንዲያና መቼም አያደርሱም።

ኢየሱስ ብቻውን በእግዚሐብሔር ስልጣን ይናገራል፣ ምክኒንቱም ኢየሱስ ብቻ ነው ሞትን ያሸነፈው። እስካሁን ድረስ መሐመድ፣ ኮንፊሸየስና ሌሎች በመቃብር በስብሰው ይገኛሉ። ነገር ግን ኢየሱስ በራሱ ስልጣን በጨካኙ የሮማውያን መስቀል ከሞተ ከሦስት ቀን በኋለ መቃብሩን ፈንቅሎ ተነስቶአል። በሞት ላይ ስልጣን ያለው ማንኛውም ሰው ትኩረታችን ሊስብ ግድ ይላል። ማንም በሞት ላይ ስልጣን ያለው ግለሰብ ሲናገር ልናደምጠው አስፈላጊ ነው።

የኢየሱስን ትንሳኤ የሚደግፈው መረጃ የሚያጥለቀልቅ ነው። በመጀመሪያ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ ምስክሮች የተነሳውን ክርስቶስ አይተዋል! እነዚህ በጣም ብዙ የዓይን ምስክሮች ናቸው። አምስት መቶ ድምፆች በቀላሉ ችላ የሚባሉ አይደሉም። ባዶውን የቀረውም የመቃብር ቦታ ጉዳይ አለ። የኢየሱስ ጠላቶች ያን ሁሉ ስለትንሳኤው የተነዛውን ወሬ የራስ ቅሉንና የበሰበሰውን አካሉን በማቅረብ በቀላሉ ያስታግሱት ነበር። ነገር ግን የሚያሳዩት ሬሳ ሊያገኙ አልቻሉም። የመቃብሩ ቦታ ባዶ ነበር! ምናልባት ደቀመዛሙርቱ ሬሳውን ሰርቀውት ይሆን? የማይመስል ነው። ይህንን መሳይ ችግር ለመከላከል ሲባል የኢየሱስ መቃብር በታጠቁ ወታደሮች ከፍተኛ ጥበቃ ሲደረግለት ነበር። የቅርብ ተከታዮቹ መያዙንና መሰቀሉን በማየት ሸሽተዋል። የተደናገጡት አሳ አጥማጆች ከፍተኛ ስልጠናና ትጥቅ ከነበራቸው ወታደሮች ጋር ግንባር ለግንባር ይገጥማሉ ማለት ፈፅሞ የሚታሰብ አይደለም። ለተጭበረበረ ነገርስ ውድ ህይወታቸውን በመሰዋት ብዙዎቹ እንደሆኑት ሰማዕታት ይሆኑ ነበርን? ቀላሉ ሃቅ ግን የኢየሱስ ትንሳኤ እንዲሁ ተነግሮ ተገልፆ የሚያልቅ መች ሆነና!

እንደገና በሞት ላይ ስልጣን ያለው ማንም ሰው ሊደመጥ ይገባል። ኢየሱስ በሞት ላይ ያለውን ሥልጣን አረጋግጧል። ስለዚህ የሚናገረውን መስማት ይገባናል። ለድነት ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ መሆኑን ራሱ ይናገራል።(ዮሐንስ 14፡ 6)። እሱ መንገድ አይደለም፣ ካሉትም ብዙ መንገዶች አንዱ አይደለም። ኢየሱስ ብቸኛ መንገድ ነው።

ይህ ብቸኛ ኢየሱስ እንዲህ ይላል “እናንተ ደካሞች፤ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደእኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” (ማቴዎስ 11፡ 28)። ይህ አስጨናቂ ዓለም ነው። ህይወትም አስቸጋሪ ነው። ብዙዎቻችን ደምተናል፣ ቆስለናል፣ ጦርነትንም እንፈራነል። ትስማማላችሁ? ስለዚህ ምን ትፈልጋላችሁ? ተሐድሶ ወይስ ተራ ሐይማኖት? ሕያው የሆነ አዳኝ ወይስ “ከሞቱት በርካታ ነቢያት” አንዱን? ትርጉም ያለው ግንኙነት ወይስ ተራ የዓምልኮ ሥነ-ሥርዓት? ኢየሱስ አማራጭ ሳይሆን ምርጫ ነው! ይቅርታን ትፈልግ እንደሆን ኢየሱስ ትክክለኛ “ሐይማኖት” ነው። (የሐዋርያት ሥራ 10፡ 43)። ከእግዚሐብሔር ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት ትፈልግ እንደሆን ኢየሱስ ትክክለኛ “ሐይማኖት” ነው። (ዮሐንስ 3፡ 16) ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝህ ተቀብለህ እምነትህን በእርሱ ላይ ጣል። ፈፅሞ አትቆጭም! ለኃጢያትህ ሥርየት በእርሱ ታመን አያሳፍርህም።

ከእግዚሐብሔር ጋር “ትክክለኛ ግንኙነት” እንዲኖርህ ከፈለግህ የናሙና ፀሎት ይኸው ቀርቦልሐል። አስታውስ ይህንን ፀሎት ወይም ሌላ ፀሎት ማቅረብ አያድንህም። በኢየሱስ ክርስቶስ መታመን ብቻ ነው ከኃጢያት የሚያድንህ። ይህንን ፀሎት የምታቀርበው በእግዚሐብሔር ላይ ያለህን እምነት ለመግለጽና ድነትን ስላስገኘልህ ምስጋናህን ለማስቀደም ነው። “እግዚሐብሔር ሆይ አንተን ስለበደልኩ ቅጣት ይገባኛል። ነገር ግነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔ የገባውን ቅጣት ስለከፈለልኝ በርሱ በማመኔ ይቅርታ ተደርጎልኛል። ለድነቴ እምነቴን ባንተ ላይ እጥላለሁ። ስለአአስደናቂው ፀጋህና ይቅርታህ እንዲሁም ስለዘለአለም ሕይወት ስጦታህ አመሰግንሐለሁ!አሜን!

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ለኔ የሚሆን ትክክለኛው ሐይማኖት የትኛው ነው?
© Copyright Got Questions Ministries