settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ምንድነው?

መልስ፤


የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የአማኞች ተስፋ ነው፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር የሚቆጣጠርበት፣ እሱም የታመነ ነው ለተስፋዎቹና በቃሉ ላሉ ትንቢቶች። በመጀመሪያ ምጽአቱ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው እንደ ሕፃን ሆኖ በቤተልሔም በረት ውስጥ ነው፣ ልክ እንደተተነበየው። ኢየሱስ አብዛኞቹን ስለ መሲሕ የተነገሩትን ትንቢቶች ፈጽሟል፣ በተወለደበት ጊዜ፣ በሕይወቱ፣ አገልግሎቱ፣ ሞቱ እና ትንሣኤው። ሆኖም፣ አንዳንድ ትንቢቶች አሉ፣ መሲሕን በተመለከተ ኢየሱስ ገና ያልፈጸማቸው። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት የክርስቶስ መመለስ ይሆናል፣ እነዚህን ቀሪዎቹን ትንቢቶች ለመፈጸም። በመጀመሪያ ምጽአቱ፣ ኢየሱስ መከራ የተቀበለ አገልጋይ ነበረ። በዳግም ምጽአቱ፣ ኢየሱስ ድል አድራጊ ንጉሥ ይሆናል። በመጀመሪያ ምጽአቱ፣ ኢየሱስ የደረሰው እጅግ ትሑት በሆነ መልኩ ነው። በዳግም ምጽአቱ፣ ኢየሱስ የሰማይ ሠራዊትን ከጎኑ አሰልፎ ነው የሚመጣው።

የብሉይ ኪዳን ነቢያት ይህንን ልዩነት በግልጽ አላስቀመጡትም፣ በሁለቱ ምጽአቶች መካከል ያለውን ልዩነት። ይህም ኢሳይያስ 7:14፣ 9:6-7 እና ዘካርያስ 14:4 ይታያል። ትንቢቶቹ ስለ ሁለት ሰዎች የሚናገሩ ከመምሰላቸው የተነሣ፣ በርካታ የአይሁድ ሊቃውንት፣ መከራን የሚቀበለው መሲሕና ድል አድራጊው መሲሕ ሁለቱም ይኖራሉ ብለው ያምናሉ። ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር አንድ መሲሕ እንደሚኖርና ሁለቱንም ሚናዎች የሚጫወት መሆኑን ነው። ኢየሱስ መከራ የሚቀበለውን መሲሕ ሚና ፈጽሟል (ኢሳይያስ ምዕራፍ 53) በመጀመሪያ ምጽአቱ። ኢየሱስ የእስራኤል አዳኝነቱንና ንጉሥነቱን ሚና በዳግም ምጽአቱ ይፈጽማል። ዘካርያስ 12፡10 እና ራዕይ 1፡7፣ ስለ ዳግም ምጽአቱ የሚገልጹ ናቸው፣ ኢየሱስ የተወጋ መሆኑን መለስ ብሎ በመጥቀስ። እስራኤልና መላው ዓለም ያዝናሉ፣ መሲሑን በመጀመሪያ ምጽአቱ ስላልተቀበሉት።

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ፣ መላእክት ለሐዋርያት አውጀዋል፣ “‘የገሊላ ሰዎች ሆይ’ አሉ፣ ‘ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን እዚህ ትቆማላችሁ? ይሄው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ የተወሰደው፣ ወደ ሰማይ ሲወሰድ እንደተመለከታችሁት ዳግም ተመልሶ ይመጣል’” (ሐዋርያት ሥራ 1፡11)። ዘካርያስ 14፡4 የዳግም ምጽአቱን ስፍራ ይገልጻል፣ ደብረ ዘይት መሆኑን። ማቴዎስ 24፡30 ያውጃል፣ “በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል።” ቲቶ 2፡13 ዳግም ምጽአቱ “የክብር መገለጥ” እንደሆነ ይገልጻል።

ዳግም ምጽአቱ እጅግ ዝርዝር በሆነ መልኩ የተገለጠው ራዕይ 19:11-16፣ ላይ ነው፣ “ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም። ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል። በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር። አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል። በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት። የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።”

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries