settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለምን?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ማንም ሰው እግዚአብሔርን አይቶ አያውቅም ይለናል (ዮሐንስ 1፡18) ያየው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ በዘጸአት 33:20, እግዚአብሔር ደግሞም፦ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም አለ።" ለምሳሌ ዘጽ 33፡11 ሙሴ እግዚአብሔርን ‹‹ፊት ለፊት›› አንዳናገረው ይናገራል፡፡ እንዴት ነው እግዚአብሔርን ሰው ፊት ለፊት አይቶት የማይድን ከሆነ እንዴት ነው ሙሴ እግዚአብሔርን ያናገረው? በዚህ ሁኔታ "ፊት ለፊት" የሚለው ሐረግ በጣም ቅርብ በሆነ ኅብረት ውስጥ እንደሚገኝ የሚጠቁሙ የንግግር ዘይቤ ነው፡፡ እግዚአብሔር እና ሙሴ እርስ በእርሳቸው የሚነጋገሩት ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው እንደሚነጋገሩ ነበር፡፡

በዘፍጥረት ምዕራፍ 32 ቁጥር 30, ያዕቆብ እግዚአብሔር እንደ መልአክ ሆኖተመለከተ፤ እግዚአብሔርን በእውነት አላየውም፡፡ የሳምሶን ወላጆች እግዚአብሔርን እንዳዩ ሲመለከቱ ደንግጠው ነበር (መሳፍንት 13፡22) ነገር ግን እንደ መልአክ ሲገለጥ አይተው ነበር፡፡ ኢየሱስ ሥጋ የሆነው አምላክ ነበር (ዮሐንስ 1፡1,14) ስለዚህ ሰዎች ሲያዩት እግዚአብሔርን ያዩ ነበር፡፡ ስለዚህ አዎ እግዚአብሔር "ይታያል" እናም ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን "ያዩታል" በተመሳሳይ ሁኔታ ማንም ሰው በክብሩ የተገለጠውን እግዚአብሔርን አይቶ አያውቅም፡፡ በወደቀው የሰው ልጅ ሁኔታችን ውስጥ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ሙሉ ለሙሉ ቢገልጥልን ተውጠን እንዲሁ እንጠፋለን፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር ራሱን የሚያጋርድ ሲሆን እርሱን "ማየት" እንድችል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔርን በሁሉም ክብሩ እና ቅድስናው እርሱን ከማየት የተለየ ነው፡፡ ሰዎች እግዚአብሄርን በራዕይ የእግዚአብሔር ምልክን የእግዚአብሔርን መገለጦች አይተዋል፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ በሙላት አላየውም (ዘጸአት 33 20)፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለምን? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries