ጥያቄ፤
ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ምንድናቸው?
መልስ፤
ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ዝርዝራቸው በመነሻ ጥቅም ላይ የዋለው በጥንት የክርስቲያን ትምህርት ነው፣ ተከታዮችን ለማስተማርና ለማስጠንቀቅ፣ የወደቀውን ሰው ኃጢአት አዝማሚያ በተመለከተ። በሰባቱ “ገዳይ” ኃጢአቶች ላይ ያለው የተዛባ መረዳት፣ እነዚህን ኃጢአቶች እግዚአብሔር ይቅር እንደማይል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ያደረገው፣ እግዚአብሔር ግልጽ ያደረገው ብቸኛው ኃጢአት ቀጣይነት ያለው አለማመን ነው፣ ምክንያቱም እሱ ብቸኛውን ይቅርታ የሚገኝበትን መንገድ ስላልተቀበለ— ኢየሱስ ክርስቶስ እና የእሱን ምትክ ሞት በመስቀል ላይ።
የሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን? አዎንም አይደለምም፣ ምሳሌ 6፡16-19 ያውጃል፣ “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፡ 1) ትዕቢተኛ ዓይን፥ 2) ሐሰተኛ ምላስ፥ 3) ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ 4) ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ 5) ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥6) በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፣ 7) በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።” ሆኖም፣ ይህ ዝርዝር አብዛኞቹ ሰዎች የሚረዱት እንደ ሰባቱ ገዳይ ኃጢአት አይደለም።
እንደ ታላቁ አቡነ ግሪጎሪ 6ኛ ክፍለ-ዘመን፣ ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች የሚከተሉት ናቸው፡ ኩራት፣ ምቀኝነት፣ በላተኝነት፣ መጎምጀት፣ ቁጣ፣ ስስት፣ እና ስንፍና። ምንም እንኳ እነዚህ ኃጢአት መሆናቸው ባይካድም፣ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ “ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች” የሚል ገለጻ አያሰጣቸውም። ልማዳዊ የሆነው የሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ዝርዝር፣ ያሉትን በርካታ የተለያዩ ኃጢአቶች ለመመደቢያ መንገድ ሆኖ ማገልገል ይችላል። ባመዛኙ እያንዳንዱን ዓይነት ኃጢአት ከሰባቱ ምድቦች በአንደኛው ማኖር ይቻላል። እጅግ ጠቃሚ የሚሆነው፣ እነዚህ ሰባት ኃጢአቶች ካሁን በኋላ “ገዳይ” አለመሆናቸውን ነው፣ ከሌላው ኃጢአት በበለጠ። ሁሉም ኃጢአት ውጤቱ ሞት ነው (ሮሜ 6፡23)። እግዚአብሔር ይመስገን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችን ሁሉ፣ “ሰባቱን ገዳይ ኃጢአቶችን” ጨምሮ ይቅር ልንባል እንችላለን (ማቴዎስ 26:28፤ ሐዋ. 10:43፤ ኤፌሶን 1:7)።
English
ሰባቱ ገዳይ ኃጢአቶች ምንድናቸው?