settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የተጋቡ ክርስቲያን ጥንዶች በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ የተፈቀደላቸው/ያልተፈቀደላቸው ምንድነው?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ይላል “መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል” (ዕብራውያን 13፡4)። ቅዱስ ቃሉ ባልና ሚስት በግብረ ሥጋ ግንኙነት ምን ማድረግ እንዳለባቸውና አንደሌለባቸው ፈጽሞ አይገልጽም። ባሎችና ሚስቶች ታዘዋል፣ “ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ (1 ቆሮንቶስ 7፡5ሀ)። ይህ ቁጥር ምናልባት በጋብቻ የሚኖረውን የግብረ-ሥጋ ግንኙነት መርሕ ያስቀምጣል። ምንም ነገር ቢደረግ በመግባባትና በስምምነት መሆን አለበት። ማንም መበረታታት ወይም መገፋፋት አይኖርበትም፣ እሱ ወይም እሷ የማይመቻቸውን ወይም ትክክል አይደለም ብለው የሚያስቡትን። ባልና ሚስት ሁለቱም አንድ ነገር ለመሞከር ቢስማሙ (ምሳሌ፣ የአፍ ግንኙነት፣ የተለያዩ አቅጣጫዎች፣ የግብረ-ሥጋ ማሳያዎች፣ ወዘተ) እንግዲያውስ መጽሐፍ ቅዱስ እንደማይችሉ ምንም ምክንያት አይሰጥም።

ጥቂት ነገሮች አሉ፣ ከግብረ-ሥጋ ግንኙነት አኳያ ለተጋቡ ጥንዶች ፈጽሞ ያልተፈቀዱ። “የመሸቃቀጥ ልምምድ” ወይም “በትርፍነት ማግኘት” (ሦስት በአንድ፣ አራት በአንድ፣ ወዘተ) ግልጽ የሆነ ዝሙት ነው (ገላትያ 5፡19፤ ኤፌሶን 5፡3፤ ቆላስያስ 3፡5፤ 1 ተሰሎንቄ 4፡3)። ዝሙት ኃጢአት ነው፣ የትዳር ጓደኛ እንኳ ቢፈቅድም፣ ቢያጸድቅም፣ ወይም ደግሞ ቢሳተፍበትም። ፖርኖግራፊ “በሥጋ ምኞትና በዓይን አምሮት” ይያዛል (1 ዮሐንስ 2፡16) እና ስለዚህ በእግዚአብሔርም ተኮንኗል። ባልና ሚስት ፖርኖግራፊን ፈጽሞ ወደ ግብረ-ሥጋ ኅብረታቸው ማምጣት አይኖርባቸውም። ከእነዚህ ከሁለቱ ዓይነቶች በቀር ቅዱስ ቃሉ ለይቶ የሚከለክለው የለም፣ ባልና ሚስት እርስ በርሳቸው እንዳያደርጉ፣ በጋራ መግባባት እስከሆነ ድረስ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የተጋቡ ክርስቲያን ጥንዶች በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ የተፈቀደላቸው/ያልተፈቀደላቸው ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries