settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ሁሉም ኃጠአት ለእግዚአብሔር እኩል ነውን?

መልስ፤


ማቴዎስ 5፡21-28 ላይ፣ ኢየሱስ ዝሙትን መፈጸምና በልብ መመኘትን እና ግድያን መፈጸምንና በልብ ጥላቻ ማድረግን እኩል አድርጎታል። ሆኖም፣ ይህ ማለት ኃጢአቶች እኩል ናቸው ማለት አይደለም። ኢየሱስ ለፈሪሳውያን ማለት የፈለገው፣ ኃጢአት ምንም ቢሆን ኃጢአት መሆኑን ነው፣ ድርጊቱን ለመፈጸም መፈለግ እንኳ፣ ያንን ባታደርገውም። የኢየሱስ ጊዜ የሃይማኖት መሪዎች ያስተምሩ የነበሩት ስለ ፈለግከው ነገር ማሰብ ልክ እንደሆነ ነበር፣ እነዛን መሻቶች እስካላደረግካቸው ድረስ። ኢየሱስ እያስገደዳቸው የነበረው እግዚአብሔር የግለሰቡ ሐሳብ ብሎም በድርጊቶቹ ላይ እንደሚፈርድ እንዲገነዘቡ ነበር። ኢየሱስ ያወጀው ድርጊቶቻችን በልባችን ያለው ውጤቶች ናቸው (ማቴዎስ 12፡34)።

ምንም እንኳ ኢየሱስ መመኘትና ዝሙት ሁለቱም ኃጢአት ቢሆኑም፣ ያ እኩል ናቸው ማለት አይደለም። ሰውን መግደል እጅግ የከፋ ነው፣ ሰውን እንዲያው ከመጥላት ይልቅ፣ ምንም እንኳ በእግዚአብሔር ዓይን ሁለቱም ኃጢአት ቢሆኑም። ኃጢአት ለማድረግ ደረጃዎች አሉ። አንዳንድ ኃጢአቶች ከሌሎች የከፉ ናቸው። በተመሳሳይ መልኩ፣ በሁለቱም፣ በዘላለማዊ መዘዝ እና በደኅንነት አኳያ ሁሉም ኃጢአት ተመሳሳይ ነው። እያንዳንዱ ኃጢአት ወደ ዘላለም ኵነኔ ያመራል (ሮሜ 6፡23)። ኃጢአት ሁሉ፣ ምንም “ትንሽ” ቢሆን፣ ወሰን የሌለውንና ዘላለማዊውን አምላክ መቃወም ነው፣ እና ስለዚህ ወሰን የሌለውና ዘላለማዊ ቅጣት ይገባዋል። በተጨማሪም፣ እጅግ “ትልቅ” የሆነ ኃጢአት የለም እግዚአብሔር ይቅር የማይለው። ኢየሱስ የሞተው የኃጢአትን ቅጣት ለመክፈል ነው (1 ዮሐንስ 2፡2)። ኢየሱስ የሞተው ለኃጢአታችን ሁሉ ነው (2 ቆሮንቶስ 5፡21)። ኃጢአት ሁሉ ለእግዚአብሔር እኩል ነውን? አዎንም አይደለምም። በአስከፊነት? አይደለም። በቅጣት? አዎን። ይቅር በመባልነት? አዎን።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ሁሉም ኃጠአት ለእግዚአብሔር እኩል ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries