ጥያቄ፤
በማጨስ ላይ የክርስቲያን አመለካከት ምንድነው? ማጨስ ኃጢአት ነውን?
መልስ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ማጨስን በቀጥታ ፈጽሞ አይጠቅስም። የሆነ ሆኖ መርሖዎች አሉ፣ በርግጥ ስለ ማጨስ ሊውሉ የሚችሉ። አንደኛ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ያዘናል፣ አካላችን በማናቸውም ነገር “እንዳይገዛ።” “ሁሉ ተፈቅዶልኛል—ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል— ምንም ነገር ግን አይሠለጥንብኝም” (1 ቆሮንቶስ 6፡12)። ማጨስ ሊካድ በማይቻል መልኩ ኃይለኛ ሱስ ነው። ኋላ ላይ በተመሳሳይ ምንባብ ይነገረናል፣ “ሥጋችሁ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ-መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን፣ እሱም በእናንተ ያለው፣ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት? የራሳችሁ አይደላችሁም፤ በዋጋ ተገዝታችኋል። ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ” (1 ቆሮንቶስ 6፡19፡20)። ማጨስ ያለ ጥርጥር ለጤናችሁ ጎጂ ነው። ማጨስ ሳንባንና ልብን እንደሚጎዳ ተረጋግጧል።
ማጨስ እንደ “ጠቃሚ” ሊታይ ይችል ይሆን (1 ቆሮንቶስ 6፡12)? ማጨስ በሥጋ እግዚአብሔርን ማክበር ማለት ይቻላልን (1 ቆሮንቶስ 6፡20)? አንድ ግለሰብ “ለእግዚአብሔር ክብር” በታማኝነት ማጨስ ይችላልን (1 ቆሮንቶስ 10፡31)? ለእነዚህ ሦስት ጥያቄዎች ምላሻቸው የሚያቃጭለው “አይደለም” ነው። በዚህ መሠረትም፣ እኛ እንደምናምነው ማጨስ ኃጢአት ነው፣ እና ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች መደረግ አይኖርበትም።
አንዳንድ ሰዎች ይሄንን አመለካከት ይቃረናሉ፣ ብዙ ሰዎች ጤናማ ያልሆነ ምግብ ይመገባሉ በሚለው ላይ በመጠቆም፣ እሱም እንደ ሱስ ሊሆን የሚችልና ለሰውነትም ጎጂ የሆነ። እንደ ምሳሌም፣ ብዙ ሰዎች በከፋ መልኩ የቡና ሱሰኛ ሆነዋል፣ በጧት አንድ ስኒ ቡና ካላገኙ እስከማይሠሩ ድረስ። ይሄ እውነት ቢሆንም፣ ያ እንዴት ማጨስን ትክክል ያደርገዋል? እሱ የእኛ ክርክር ነው፣ ክርስቲያኖች በላተኝነትንና ከመጠን ያለፈ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብን ያስወግዱ ዘንድ። አዎን፣ ክርስቲያኖች ዘወትር ግብዞች ናቸው፣ አንዱን ኃጢአት በመኮነንና ሌላውን ኃጢአት በመሸፈን፣ ነገር ግን እንደገና ይህም ማጨስን እግዚአብሔርን ማክበር አያደርገውም።
ሌለኛው ክርክር ይህንን የማጨስ አመለካከት በመቃወም፣ ብዙ መልካም ሰዎች አጫሾች ነበሩ፣ እንደ ታዋቂው የብሪታንያ ሰባኪ ሲ.ኤች. ስፐርጂኦን፣ ሲጋራ በማጨሱ የሚታወቀው። እንደገናም፣ ይህም ክርክር ሚዛን እንዳለው አናምንም። ስፐርጂኦን በማጨሱ ስሕተተኛነቱን እናምናለን። በሌላ መልኩ እሱ መልካም ሰውና አስደናቂ የእግዘዚአብሔር ቃል ሰባኪ አልነበረምን? እንዴታ! ያስ የእሱን ድርጊቶችና ጠባዮች ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ያደርጋቸዋልን? አይደለም!
ማጨስን ኃጢአት ብሎ በማስቀመጥ፣ አማኞች ሁሉ አልዳኑም ማለታችን አይደለም። በርካታ እውነተኛ በኢየሱስ ክርስቶስ አማኞች አሉ፣ የሚያጨሱ። ማጨስ ግለሰቡን ከመዳን አያግደውም። አልያም እሱ ግለሰቡን ደኅንነተቱን እንዲያጣ አያደርገውም። ማጨስ ከሌሎቹ ኃጢአቶች የበለጠ ይቅርታ የማይባል አይደለም፣ ክርስቲያን ለሆነ ሰውም ሆነ ኃጢአቱን/ቷን ለእግዚአብሔር ለሚናዘዝ (1 የዮሐንስ 1፡9)። በተመሳሳይ ጊዜ፣ በጽናት የምናምነው ማጨስ ኃጢአት ነው፣ ይቅርታን ማግኘት ያለበት፣ በእግዚአብሔር ርዳታም የሚተው።
English
በማጨስ ላይ የክርስቲያን አመለካከት ምንድነው? ማጨስ ኃጢአት ነውን?