ጥያቄ፤
ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው ብሎ ማለት ምንድን ነው?
መልስ፤
በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ 88 ጊዜ የሰው ልጅ ተበሎ ተጠርቶአል፡፡ የመጀመሪያው የሰው ልጅ የሚለው ትርጉም በዳንኤል 7፡13- 14 ያለውን ያመለክታል፡ ‹‹በሌሊት ራእይ አየሁ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።›› የሰው ልጅ የሚለው የሚሰህ መገለጫ ነው፡፡ ኢየሱስ ክብር ግዛት መንግስትም የተሰጠው ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ይህ ቃል ሲጠቀም የሰው ልጅ የመሆኑን ለራሱ የተነገረውን ትንቢት ለማመልከት ነው፡፡ በዚያን ዘመን የነበሩ አይሁዶች ከቃሉ በቅርብ ይረዱታል እንዲሁም ማንን እንደሚያመለክት፡፡ ኢየሱስ ራሱን መሲህ እንደሆነ እየተናገረ ነው፡፡
ሁለተኛው የሰው ልጅ የሚለ ቃል ትርጉም፤ ኢየሱስ በትክክል ሰው መሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር ነብዮን እዝቅኤል የሰው ልጅ እያለ 93 ጊዜ ጠርቶታል፡፡ እግዚአብሔር በቀላሉ ሰው እያለ ሲጠራው ነው፡፡ የሰው ልጅ ሰው ነው፡፡ ኢየሱስ ፍጹም አምላክ ነው (ዮሐ 1፡1) ግን ደግሞ ሰው ነው (ዮሐ 1፡14)፡፡ የመጀመሪያ ዮሐ 4፡2 ሲናገር፡ ‹‹የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥›› አዎን ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው፤ በማንነቱ ሰብአዊ ፍጡር ነው፡፡ በማጠቃለያ የሰው ልጅ የሚለው ቃል ኢየሱስ መሲህ እደሆነ ያመለክታል እንደሁም በትክክል ሰው ነው፡፡
English
ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው ብሎ ማለት ምንድን ነው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?