ጥያቄ፤
በልሣኖች የመናገር ስጦታ ምንድነው?
መልስ፤
የመጀመሪያው በልሣኖች የመናገር ክስተት የሆነው በጴንጤ ቆስጤ ቀን በሐዋሪያት ሥራ 2፤1-4 ነው፡፡ ሐዋሪያቶች ወጥተው ወንጌልን ለተሰበሰቡት በራሳቸው ቋንቋዎች እየነገሯቸው፤“የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።” (የሐዋሪያት ሥራ 2፤11) የግሪኩ ቃል ልሳኖችን ቃል በቃል የተረጎመው “ቋንቋዎች” በማለት ነው፡፡ ስለዚህ የልሳኖች ሥጦታ አንድ ያንን ቋንቋ የሚናገረው ሌላውን ሰው ለማገልገል በማያውቀው ቋንቋ መናገር ነው፡፡ በ1ኛ ቆሮንቶስ 12 እስከ 14 ምዕራፎች ጳውሎስ ድንቅ ስጦታዎችን “አሁን ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ ወይም በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ?” (1ኛ ቆሮንቶስ 14፤6) እያለ ያነሳል፡፡ እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስ እና በሐዋሪያት ሥራ ውስጥ ከተገለጸው ከልሳኖች ቋንቋ ጋር በሚስማማ መልኩ በልሳኖች መናገር አንድ በራሱ ወይም በራሷ ቋንቋ የእግዚአብሔርን መልዕክት በመስማት ላይ ላለ/ላለች ጠቃሚ ነው፤ ካልተተረጎመ ግን ለማንኛውም ሰው ጥቅም የለውም፡፡
ልሳኖችን የመተርጎም ስጦታ ያለው ሰው (1ኛ ቆሮንቶስ 12፤30) ምንም እንኳን በመነገር ላይ የነበረውን ቋንቋ ባያውቅም የልሳን ተናጋሪው በመናገር ላይ የነበረውን ነገር መረዳት ይችላል፡፡ ልሳን ተርጓሚው ልሳኖቹን የሚናገረውን ሰው መልዕክት ሁሉ ሰው መረዳት እንዲችል ለእያንዳንዱ ሰው ይናገራል፡፡ “ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።”(1ኛ ቆሮንቶስ 14፤13)፡፡ የማይተረጎመቱን ልሳኖች በተመለከተ የጳውሎስ ማጠቃለያ ጠንካራ ነበር፤ “ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።” (1ኛ ቆሮንቶስ 14፤19)
በልሣኖች የመናገር ስጦታ ለዚህ ዘመን ነውን? ምንም እንኳን መሻሩ በ1ኛ ቆሮንቶስ 13፤10 ፍጹም የሆነው ከመምጣቱ ጋር ቢገናኝም 1ኛ ቆሮንቶስ 13፤8 የልሳኖች ስጦታ መሻሩን ይጠቅሳል፡፡ አንዳንዶች የትንቢትን እና የዕውቀትን “መሻር” እና “ፍጹም” የሆነው ከመምጣቱ በፊት “የሚሻሩቱን ልሳኖች” ለልሳኖች መሻር እንደ ማስረጃ በማስመልከት የተወሰኑቱ በግሪኩ ግስ አመጣጥ ላይ ወዳለው ልዩነት ያመለክታሉ፡፡ መሆን ሲቻል እንኳን ይኸ ከምንባቡ በጣም ግልጽ አይደለም፡፡ በተጨማሪም የተወሰኑቱ በልሳኖች መናገር እየመጣ ላለው የእግዚአብሔር ፍርድ ምልክት እንደነበር ትንቢተ ኢሳይያስ 28፤11 እና ትንቢተ እዩኤል 2፤28-29 ወደ መሳሰሉት ምንባቦች እንደ ማስረጃ ያመለክታሉ፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 14፤22 ልሳኖች “ለማያምኑት ምልክት” እንደሆነ ይገልጻል፡፡ በዚህ ክርክር መሠረት በልሳኖች የመናገር ስጦታ እግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስን መስዕነት ባለመቀበላቸው እስራኤላውያንን ሊፈርድባቸው እንዳለ ለአህሁዶች ማስጠንቀቂያ ነበር፡፡ ስለዚህ በእርግጥ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በፈረደበት ጊዜ (በ70 ዓመተ ዓለም የኢየሩሳሌም በሮማውያኖች መውደም) የልሳኖች ስጦታ የታሰበለትን ዓላማ አላገለገለም ነበር፡፡ ይህ አመለካከት የሚቻል ቢሆንም የመጀመሪያው በልሳኖች የመሞላት ዓላማ የግድ መሻሩን ተፈላጊ አያደርገውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በልሳኖች የመናገር ስጦታ እንደተሻረ በመደምደም አያውጅም፡፡
በተመሳሳይ ጊዜ በልሳኖች የመናገር ስጦታ ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራ ቢሆን ኖሮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በሚስማማ መልኩ ይደረግ ነበር፡፡ እውነት እና ግልጽ ቋንቋ ይሆናል (1ኛ ቆሮንቶስ 14፤10)፡፡ ሌላ ቋንቋ (የሐዋሪያት ሥራ 2፤6-12) ከሚናገር ሰው ጋር ለመነጋገር ዓላማ የሚጠቅም ይሆናል:: እግዚአብሔር በሐዋሪያው ጳውሎስ በኩል ከሰጠው ትዕዛዝ ጋር የሚስማማ ይሆናል፤ “በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤ የሚተረጉም ባይኖር ግን በማኅበር መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር።” (1ኛ ቆሮንቶስ 14፤27-28) በተጨማሪም በ1ኛ ቆሮንቶስ 14፤33 መሠረት ይሆናል፤ “እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።”
እግዚአብሔር በእርግጠኝነት ሌላ ቋንቋ ከሚናገር ሰው ጋር መግባባት እንዲያስችለው ወይም እንዲያስችላት ለአንድ ሰው በልሳኖች የመናገርን ስጦታ ሊሰጥ ይችላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በማካፈል ሉዓላዊ ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 12፤11)፡፡ ሚሲዮኖች ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት ካልሄዱ እና ወዲያው በራሳቸው ቋንቋ ለሰዎች መናገር ቢችሉ ምን ያህል የበለጠ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ እስኪ አስብ፡፡ ሆኖም ግን አግዚአብሔር ይህንን የሚያደርግ አይመስልም፡፡ ምንም አብዝቶ ጠቃሚ የሚሆኑ እንኳ ቢሆኑም ልሳኖች በአዲስ ኪዳን በሆነው መልኩ የሚከሰቱ አይመስልም፡፡ በልሳኖች የመናገርን ስጦታ እንተገብራለን የሚሉ ብዙኃኑ የአማኞች ክፍል ከላይ ከተጠቀሱት ከቅዱሳን መጽሐፍት ጋር በሚስማማ መልኩ ያንን አያደርጉም፡፡ እነዚህ እውነታዎች ለዛሬይቱ ቤተክርስቲያን የልሳኖች ስጦታ ተሽረዋል ወይም ቢያንስ በእግዚአብሔር ዕቅድ ብርቅ ነው ወደሚለው ድምዳሜ ይመራል፡፡
English
በልሣኖች የመናገር ስጦታ ምንድነው?