settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መንፈሳዊ ዕድገት ምንድነው?

መልስ፤


መንፈሳዊ ዕድገት በተሻለ ኢየሱስ ክርስቶስን የመምሰል ሂደት ነው። እምነታችንን በኢየሱስ ላይ ስናውል፣ መንፈስ ቅዱስ እሱን እንድንመስል ሂደቱን መሥራት ይጀምራል፣ የእርሱን መልክ እንድንመስል በማጽናት። መንፈሳዊ ዕድገት በተሻለ የተገለጸው 2 ጴጥሮስ 1፡3-8 ላይ ነው፣ እሱም የሚነግረን ያለንን የእግዚአብሔር ኃይል “የሚያስፈልገንን ሁሉ” መልካምን ሕይወት ለመኖር፣ ይኸውም የመንፈሳዊ ዕድገት ግብ የሆነ። የሚያስፈልገን የሚመጣው “እሱን በማወቃችን፣” እንደሆነ ተገንዘቡ፣ እሱም የሚያስፈልገንን የምናገኝበት ቁልፍ ነው። እሱን ማወቃችን የሚመጣው ከቃሉ ነው፣ እሱም ለመንጻታችንና ለዕድገታችን የተሰጠን።

ገላትያ 5፡19-23 ሁለት ዝርዝሮች አሉ። ከቁ. 19-21 “የሥጋ ሥራዎችን” ይዘረዝራል። እነዚህም ወደ ክርስቶስ መዳን ከመምጣታችን በፊት በሕይወታችን የሚገለጡት ነገሮች ናቸው። የሥጋ ሥራዎች ልንናዘዛቸው፣ ንስሐ ልንገባ፣ እና በእግዚአብሔር ርዳታ ልናሸንፋቸው የሚገቡ ድርጊቶች ናቸው። መንፈሳዊ ዕድገትን እንደምንለማመድ፣ “የሥጋ ሥራዎች” በሕይወታችን እየቀነሱ፣ እየቀነሱ ይሄዳሉ። ሁለተኛው ዝርዝር “የመንፈስ ፍሬ” ነው (ቁጥር 22-23)። እነዚህ አሁን የሕይወታችን ባሕርይ መሆን ያለባቸው ናቸው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ደኅንነትን ካገኘን በኋላ። መንፈሳዊ ዕድገት የሚገለጸው የመንፈስ ፍሬዎች በአማኙ ሕይወት ውስጥ እየጨመሩ ሲታዩ ነው።

የደኅንነት መለወጥ ሲከናወን፣ መንፈሳዊ ዕድገት ይጀምራል። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይኖራል (ዮሐንስ 14፡16-17)። በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ነን (2 ቆሮንቶስ 5፡17)። አሮጌው፣ ኃጢአተኛው ተፈጥሮ ለአዲሱ መንገድ መልቀቅ ይጀምራል፣ ክርስቶስን ለሚመስለው ተፈጥሮ (ሮሜ 6-7)። መንፈሳዊ ዕድገት የሕይወት ዘመን ሂደት ነው፣ እሱም የሚወሰነው የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናታችንና በመተግበራችን ነው (2 ጢሞቴዎስ 3፡16-17) እና በመንፈስ እንደ መራመዳችን (ገላትያ 5፡16-26)። መንፈሳዊ ዕድገትን እንደምንፈልግ፣ ወደ እግዚአብሔር መጸለይና ጥበብን መለመን ይኖርብናል፣ እሱ እንድናድግ በሚፈልግበት አካባቢ። እግዚአብሔርን ልንለምነው እንችላለን በእርሱ ላይ ያለን እምነትና እውቀት እንዲጨምር። እግዚአብሔር በመንፈስ እንድናድግ ይሻል፣ እሱም መንፈሳዊ ዕድገትን እንድንለማመድ የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶናል። በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ፣ ኃጢአትን ድል ልናደርግ እንችላለን፣ እንዲሁም በተሻለ አዳኛችንን፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንመስል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መንፈሳዊ ዕድገት ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries