ጥያቄ፤
ወደ ደኅነት የሚወስዱን ደረጃዎች ምንድን ናቸው?
መልስ፤
ልክ በእስልምና እንዚያን አምስት ትዕዛዞች በመፈጸም መዳን ይቻላል ተብሎ አንደሚያመነው ሁሉ ብዙ ሰዎች የደኅንነትን መንገድ እየፈለጉ ናቸው፡ ፡፡ በእስልምና አምስቱን ትዕዛዞች በመፈጸም ድኅነት እንደሚገኝ ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም ደረጃ በደረጃ በሂደት ድኅነትን ማግኘት በአብዛኛው ክርስቲያኖች ተቀባይነት ስላለው በሂደት በሚገኝ ደኅነት አስተሳሰብ ስህተት ይደረጋል፡፡ የሮማ ካቶሊክ 7 የቁርባን /sacraments /ስርዓቶች አሉአቸው፡፡ የተለያዩ ክረስቲያን ቤተእምነቶች በውሃ መጠመቅን ግልጽ ኑዛዜን ከኃጢያት መመለስ በልሳን መናገር የመሳሰሉትን ወደ ደኅነት የሚወስዱ አድርገው ጨምረው ይቀበላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ለደህንነት አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው፡፡ የእስሪ ቤቱ አለቃ ጳውሎስን ሲጠይቀው ‹‹ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።›› (ሥራ 16፡30-31)
በኢየሱስ ክረስቶስ አዳኝነት ማመን ብቸኛው የድኅነት መንገድ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት በጣም ግልጽ ነው፡፡ ሁላችንም እግዚአብሔርን በድለናል (ሮሜ 3፡23)፡፡ በኃጢያታችን ምክንያት ለዘለአለም ከእግዚአብሔር መለየት ይገባናል (ሮሜ 6፡23)፡፡ እረሱ እግዚአብሔር ለእኛ ባለው ፍቅር (ዮሐ 3፡16) እግዚአብሔር ልጁን ሰጥቶን በእኛ ቦታ እንዲሞት አድርጎታል፤ እኛ የሚገባንን ቅጣት ወስዶልና (ሮሜ 5፡8፤ 3ቆሮ 5፡21)፡፡ እግዚአብሔር የኃጢያት ይቅርታን እና ዘላለማዊ ህይወትን ሉሁሉም ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሱስ የማዳን ስራ በጸጋው ለመስጠት ለሁሉም ተስፋን ሰጥቶአል (ዮሐ 1:12? 3:16; 5:24? ሥራ 16:31).
ድኅነት የሆኑ ቅድመ ተከተሎችን መፈጸም አይደለም፡፡ አኦዎን ክርስቲያን መጠመቅ አለበት፤ አዎን ክርስቲያን ከኃጢያት መመለስ አለበት፡፡ አዎን ክርስቲያኖች ህይወታቸውን እግዚአብሔርን ለመታዘዝ አሳልፈው መስጠት አለባቸው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ ድኅነትን የማግኛ ቅድመ ተከተሎች አይደሉም፡፡ ደኅነትን የማግኝት ውጤት ናቸው፡፡ በኃጢያታችን ምክንያት በምንም አይነት ሁኔታ ድኅነትን ልናገኝ አንችልም፡፡ 1000 መንገዶችን ልንከተል እንችላለን ግን በቂ አይሆኑም፡፡ ለዚህ ነው ኢየሱስ በእኛ ቦታ መሞት የነበረበት፡፡ እኛ በፍጹም ለእግዚአብሔር እዳችንን መከፈል አንችልም ነበር ወይንም ራሳችንን ከኃጢያት ማንጻት አንችልም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ብቻ ነበር ድኅነታችንን እውን ሊያደረገው የሚችለው እናም አደረገው፡፡ እግዚአብሔር ራሱ የቅድመ ተከተል ደረጃውን ለሚቀበለው ሁሉ ድኅነትን በማዘጋጀት ፈጸመው፡፡
ደኅነት የኃጢያት ይቅርታን ማግኘት በደረጃ በሂደት የሚገኝ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝ አድርጎ በመቀበል ሁሉንም የደኅንነት ሥራ እንደሰራልን በማመን የሚገኝ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚጠይቀን አንድ ነገር ብቻ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝ አድርጎ መቀበል እና እርሱን ብቻ የዘላለም ህይወት መንገድ መገኛ አድርጎ ማመን፡፡ ክርስትናን ከሌሎች የእምነት ክፍሎች የሚለየው ይሄ ነው ሌሎቹ ሁሉ ደኅነትን ለማግኘት የግድ መከተል የሚገባንን ደረጃዎች የሚሉት አሏቸው፡፡ የክርስትና እምነት የሚቀበለው እግዚአብሔር ሁሉንም የድኅነት መንገድ ፈጽሞታል፡፡ እንዲሁ በእምነት ብቻ እንድንቀበል ጠርቶናል፡፡
English
ወደ ደኅነት የሚወስዱን ደረጃዎች ምንድን ናቸው?