settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳቶች ወይም አካልን ስለመብጣት ምን ይላል?

መልስ፤


የብሉይ ኪዳን ህግ እስራኤላውያንን “ስለ ሞተውም ሥጋችሁን አትንጩ፥ ገላችሁንም አትንቀሱት እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” ብሎ አዟቸዋል (ኦሪት ዘሌዋውያን 19፡28)፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ዛሬ አማኞች ከብሉይ ኪዳን ሕግ በታች ባይሆኑም (ወደ ሮሜ ሰዎች 10፤4፤ ወደ ገላቲያ ሰዎች 3፤23-25፤ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፤15) ንቅሳትን በተመለከተ በንቅሳት ላይ ሕግ የመኖሩ እውነታ ጥቂት ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡ አዲስ ኪዳን አማኝ ንቅሳት ሊኖረው ወይም ላይኖረው ስለሚገባው ምንም ነገር አይልም፡፡

ከንቅሳትና ከአካል መብጣት ጋር በተያያዘ ጥሩ የሚሆነው መልካም በሆነ አስተሳሰብ እግዚአብሔር ያን ለየት ያለውን ተግባር እንዲባርከው ለመጠየቅ እና ለራሱ መልካም ዓላማ እንዲጠቀምበት በታማኝነት ለመወሰን መቻላችንና አለመቻላችን ነው፡፡ “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።” (1ኛ ቆሮንቶስ 10፡31)፡፡ አዲስ ኪዳን በንቅሳቶች ወይም አካል በመብጣት ላይ ምንም አላዘዘም፤ ነገር ግን በተጨማሪ እግዚአብሔር ንቅሳትንም ሆነ አካልን መብጣት እንዲኖረን መፈለጉን እንድናምን ምንም ዓይነት ምክንያት አይሰጠንም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ለይቶ በማይናገርበት ጉዳይ ላይ ጠቃሚ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ እግዚአብሔርን ነገሩ ያስደስተው እንደሆነና እንዳልሆነ ለጥርጣሬ ዕድል ካለ በዚያ ተግባር ውስጥ አለመሳተፉ እጅግ ተመራጭ ነው፡፡ ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡23 በእምነት ያልሆነ ሁሉ ኃጥአት እንደሆነ ያን ያስታውሰናል፡፡ ሰውነታችንም ሆነ ነፍሳችን እንደተዋጀ እና ለእግዚአብሔር የተገባ እንደሆነ ልናስታውስ ይገባናል፡፡ ምንም እንኳን 1ኛ ቆሮንቶስ 6፤19-20 በቀጥታ ለንቅሳቶች ወይም ሰውነትን ለመብጣት በቀጥታ ተግባራዊ ባይሆንም መርህን ይሰጠናል፣ “ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” ይህ ትልቅ እውነት በምናደርገው እና በሰውነቶቻችን ወዴት መሄድ ባለብን ነገር ላይ እውነተኛ አመለካከት ሊኖረው ይገባል፡፡ ሰውነታችን የእግዚአብሔር ከሆነ በንቅሳቶች ወይም ሰውነትን በመብጣት “ምልክት ከማድረጋችን” በፊት የእርሱን ግልጽ “ፈቃድ” ማግኘታችንን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳቶች ወይም አካልን ስለመብጣት ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries