ጥያቄ፤
እውነተኛ ኃይማኖት ምንድን ነው?
መልስ፤
ኃይማኖት እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል‹‹በእግዚአብሔር ማመን አምልኮ የሚገባው እንደሆነ ማመን፤ በአብዛኛው ጊዜ በመንፈሳዊ ስርዓት ንክኪ›› ወይንም ‹‹ቀጥተኛ የሆነ የእምነት ስርዓት፤ አምልኮ …ወዘተ፡፡ በአብዛኛው ጊዜ የስነ ምግባር ህግን ያካትታል፡፡›› 90 በሞቶ የአለም ህዝብ ለሃይማኖት ራሱን የሰጠ ነው፡፡ ችግሩ ግን ያሉት እጅግ ብዙ የሆኑ ኃይማኖቶች ናቸው፡፡ ትክክለኛ ሃይማኖት ምንድን ነው? እውነተኛ ሃይማኖት ምድን ነው?
በኃይማኖት ውስት ሁለት የታወቁ ነገሮች ህግጋትና ስርዓቶች ናቸው፡፡ አንዳንድ ኃይማኖቶች ከትዕዛዛት ዝርዝር ውጪ ባዶ ናቸው፤ አድርጉና አታድርጉ፤ አንድ ሰው ታማኝ ሃይማኖተኛ እንዲሆን ትዕዛዛቱን መፈጸም አለበት፤ ይህን ከአደረገ በዛ ሃይማኖት ባለው አምላክ ፊት ትክከል ይሆናል፡፡ ሁለት ህግጋትና ትዕዛዝ መሰረት ያደረጉ ኃይማኖቶች የአይሁድ ሃይማኖትና እስልምና ናቸው፡፡ እስልምና መፈጽም ያለባቸው አምስቱ አህማድ ህጎች የሚባሉ አሉአቸው፡፡ አይሁዶች በመቶዎች የሚቆጠሩ መጠበቅ የሚገቡ ህግጋቶች ለማዶች አሉአቸው፡፡ ሁለቱም ኃይማኖቶች በተወሰነ መልኩ አንድ ሰው የሃይማኖቱን ህግጋቶች በመጠበቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል ብለው ያምናሉ፡፡
ሌሎች ኃይማኖቶች ክህግጋት ይልቅ መፈጽም በሚገባቸው ስርዓቶች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ መስዋዕቶችን በመፈጽም ተግባሮችን በማድረግ ስርዓቱን በመካፈል ምግቡን በመመገብ …ወዘተ ያ ሰው ተቀባይነት ያገኛል፡፡ ካቶሊኮችን እንደዚህ አይነቱን ነገር እጻናትን በማጥመቅ፤ በጋራ በመውሰድ ኃጢያትን ለካህን በመናዘዝ በሰማይ ላሉ ቅዱሳን ጸሎትን በመጸለይ ከሞት በፊት በክህን በቀባት ወዘተ በመፈጸም እነዚህን የሚያደርገውን ሰው እግዚአብሔር በሰማይ ይቀበለዋል፡፡ በደሂዝም እና ሂንዲዩዚም በተመሳሳይ መልኩ ስርዓቶችን መሰረት ያደረጉ ኃይማኖቶች ናቸው በተወሰነ መልኩ ደግሞ ስርዓትና ህግን የሚያደርጉ ተደርገው የሚቆጠሩ ናቸው፡፡
እውነተኛ ኃይማኖት ህግጋትንም ሆነ ሃይማኖታዊ ስርዓቶችን መሰረት ያደረገ አይደለም፡፡ እውነተኛ ኃይማኖት ከእግዚአብሔር ጋር ህብረትን ማድረግ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር መለየቱና ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ እንደሚያስፈልገው እነዚህን ሁለቱን በአብዛኛው ሁሉም እምነቶች የሚቀበሉአቸው ናቸው፡፡ የተሳሳቱ ሃይማኖቶች እነዚህን ሰዎች ህግጋትና ስርዓትን በፈጸም እንደዚህን ችግሮች ሊፈቱአቸው ያስባሉ፡፡ እውነተኛ ሃይማኖት ችግሩን እግዚአብሔር ራሱ በሰራው ልዩነቱን ያጠፋዋል ብለው ይቀበላሉ፡፡ እውነተኛ ኃይማኖቶች የሚከተለውን ይቀበላሉ፡
• ሁላችንም ኃጢያትን ሰርተናል በኃጢያታችንም ከእግዚአብሔር ተለይተናል፡፡ (ሮሜ 3፡23)
• ካልተከፈለ የኃጢያት ዋጋው ሞትና እና ለዘለአለም ከእግዚአብሔር መለየት ነው (ሮሜ 6፡26)፡፡
• መለኮት በኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ አካል በመልበስ ኢየሱስ በእኛ ፈንታ ሞቶአል፤ እኛ የሚገባንን ቅጣት ተቀጥቶልናል የእርሱን ሞት ለኃጢያታችን ቅጣት በቂ መሆኑን ለማሳየት ከሙታን ተነስቶአል፡፡ (ሮሜ 5:8? 1 ቆሮ 15:3-4? 2 ቆሮ 5:21).
• ኢየሱስ አዳኝ አድርገን ብንቀበል ሞቱም ለኃጢያታችን በቂ መስዋዕት እንደሆነ ብናምን ይቅር እንባላለን እንድናለን ትጅተን ከእርሱ ጋር እንታረቃለን በእግዚአብሔርም እንጸድቃለን(ዮሐ 3:16? ሮሜ 10:9-10? ኤፌ 2:8-9).
እውነተኛ ሃይማኖት ህግና ስርዓቶች አሉት ግን መሰረታዊ ልዩነት አለው፡፡ በእውነተኛ እምነተ ህግና ስርዓት እግዚአብሔር ስላዘጋጀው ደህንነት ምላሽ የሚፈጸሙ ናቸው እንጂ ድኅነትን ለማገኘት የሚደረጉ አይደሉም፡፡ እውነተኛ ሃይማኖተ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ ክርስትና ሊፈጸሙ የሚገቡ ህጎች አሏአቸው(አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትዋሽ ወዘተ) የሚፈጸሙ ስርዓቶችም አሉአቸው (በውሃ ውስጥ በመጥለቅ ጥምቀት የጌታዕራት)፡፡ እነዚህን ህግጋቶችን መፈጸም አንድን ሰው እግዚአብሔር እንዲቀበለው አያደርገውም፡፡ ይልቁን ህግና ትዕዛዛትን በጠበቅ ከጌታ ጋር ህብረትን የማድረግ ውጤት ናቸው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በጸጋው ኢየሱስ ብቻውን ያድናል፡፡ የተሳሰቱ ኃይማኖቶች ህግና ስርዓትን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ይፈጽማሉ፡፡ እውነተኛ እምነት ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው በመቀበል እውነተኛ ህብረት ከእግዚአብሔር ጋር ይኖራቸዋል ፤ ህግጋቱንና ስርዓቶቹንም ለእግዚአብሔር ባላቸው ፍቅርና ወደ እርሱ የበለጠ ለመቅረብ በመፈለግ ይፈጽሙአቸዋል፡፡
English
እውነተኛ ኃይማኖት ምንድን ነው?