settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ቤተ-ክርስቲያን ምንድን ናት?

መልስ፤


ብዙ ሰዎች ዛሬ ቤተ-ክርስቲያንን የሚረዱት እንደ ሕንፃ ነው።ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቤተ-ክርስቲያን መረዳት አይደለም። “ቤተ-ክርስቲያን” የሚለው ቃል የመጣው ekklesia (ኢክሌሲያ) ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን፣ ትርጓሜውም “ጉባኤ” ወይም “የተጠሩ” ማለት ነው። የቤተ-ክርስቲያን ሥረ-ፍቺ ስለ ሕንፃው አይደለም፣ ስለ ሰዎች እንጂ። እሱ ውስጠ-ወይራ ነው፣ ማለትም ሰዎችን የትኛውን ቤተ-ክርስቲያን እንደሚካፈሉ ስትጠይቋቸው፣ አዘውትረው የሚገልጹት ሕንፃውን ነው። ሮሜ 16፡5 ይላል “…በቤታቸው ላለች ቤተ-ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።” ጳውሎስ የሚጠቅሰው በቤታቸው ያለችን ቤተ-ክርስቲያን ነው— የቤተ-ክርስቲያንን ሕንፃ ሳይሆን፣ የአማኞችን አካል እንጂ።

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ነች፣ እሱም ራስ የሆነባት። ኤፌሶን 1:22-23፣ “ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።” የክርስቶስ አካል በሁሉም የኢየሱስ ክርስቶስ አማኞች የተሠራ ነው፣ ከጰንጠቆስጤ ቀን አንሥቶ (ሐዋርያት ሥራ 2) ክርስቶስ እስከሚመለስ ድረስ። የክርስቶስ አካል ከሁለት ገጽታዎች ነው የተሠራችው፡

1) ሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የግል ግንኙነት ያላቸውን ሁሉ የያዘችዋ። “አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።” (1 ቆሮንቶስ 12፡13)። ይህ ቁጥር የሚለው ማናቸውም የሚያምን ሰው የክርስቶስ አካል ብልት መሆኑን እና የክርስቶስን መንፈስ እንደማስረጃ መቀበሉን ነው። ሁለንተናዊቷ የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ደኅንነትን የተቀበሉ ሁሉ ናቸው።

2) የአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ገላትያ 1፡1-2 ላይ ተገልጻለች፡ “ጳውሎስ፣ ሐዋርያ… እና ከእኔ ጋር ያሉ ወንድሞች፣ በገላትያ ላሉት አብያተ-ክርስቲያናት።” እዚህ የምናየው በገላትያ አውራጃ በርካታ አብያተ-ክርስቲያናት እንደነበሩ ነው— አጥቢያ አብያተ-ክርስቲያናት ብለን የምንጠራቸው። ባፕቲስት ቤተ-ክርስቲያን፣ ሉተራን ቤተ-ክርስቲያን፣ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን፣ ወዘተ…ቤተ-ክርስቲያን አይደለም፣ እንደ ሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን— ነገር ግን አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ነው፣ አጥቢያዊ የአማኞች አካል። ሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን የተሠራችው ከእነዚህ የክርስቶስ ከሆኑት እና ለደኅንነት እሱን ከሚያምኑት ነው። እነዚህ የሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን አባላት ከአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ኅብረት ማድረግና መንጻት ይጠበቅባቸዋል።

በማጠቃለያም፣ ቤተ-ክርስቲያን ሕንፃ ወይም ክፍለ ሃይማኖት አይደለችም። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቤተ-ክርስቲያን የክርስቶስ አካሉ ነች— ለደኅንነት በኢየሱስ ክርስቶስ እምነታቸውን ያኖሩ እነሱ (ዮሐንስ 3:16፤ 1 ቆሮንቶስ 12:13)። አጥቢያ አብያተ-ክርስቲያናት የሁለንተናዊዋ ቤተ-ክርስቲያን አባላት ስብስቦች ናቸው። አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን የሁለንተናዊቷ ቤተ-ክርስቲያን አባላት በሙላት “የአካሉን” መርሖዎች የሚተገብሩበት ነው፣ 1ቆሮንቶስ ምዕራፍ 12 ላይ ያለውን፡ ማበረታታት፣ ማስተማር፣ እና እርስ በርስ መገነባባት፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እውቀትና ጸጋ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ቤተ-ክርስቲያን ምንድን ናት?
© Copyright Got Questions Ministries