ጥያቄ፤
ስትሞት ወዴት ነው የምትሄደው?
መልስ፤
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ነው የሚያስቀምጠው በመጨረሻ ስለምትሄድባቸው ቦታዎች የሚያስቀምጠው ሁለት አማራጭ ብቻ ነው ይህውም ሲኦል ወይንም መንግስተ ሰማይ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስትሞት የምትሄድበትን መወሰን እንደምትችል በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ እንዴት? ንባብህን ቀጥል፡፡
የመጀመሪያው ችግር ሁላችንም ኃጢያተኞች ነን (ሮሜ 3፡23)፡፡ ሁላችንም ስህተት አድርገናል ክፉ ወይንም ተክክል ያልሆነ ነገር (መክ 7፡20)፡፡ ኃጢያታችን ከእግዚአብሔር ለይቶናል ይህ ደግሞ ካልተፈታ ኃጢያታችን ለዘለአለም ከእግዚአብሔር የተለየን ያደርገናል (ማቲ 25፡46፤ ሮሜ 6፡23)፡፡ ይህ ዘላለማዊ የሆነ ከእግዚአብሔር መለየት ሲኦል ነው፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘላለማዊ የእሳት ባህር ነው (ራዕ 20፡14-15)፡፡
መፍትሄው፤ መለኮት ኢየሱስ በለበሰው አካል ሰው ሆነ (ዮሐ 1:1, 14? 8:58? 10:30). ኃጢያት የሌለበት ህይወት ኖረ (1 ጴጥ 3:22? 1 ዮሐ 3:5) ራሱን በእኛ ፈንታ መስዋዕት አደረገ (1 ቆሮ 15:3? 1 ጴጥ 1:18–19). ሞቱም የእኛ የሞት ፍርድ ቅጣት ከፈለ (2 ቆሮ 5:21). እግዚአብሔር አሁን ይቅርታንና ደህንነትን በስጦታ ሰጥቶናል፡፡ (ሮሜ 6:23) በእምነት መቀበል ደግሞ አለብን (ዮሐ 3:16? ኤፌ 2:8–9). "በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።" (ሥራ 16:31).
ስትሞት ወዴት ነው የምትሄደው? የአንተ ምርጫ ነው፡፡ እግዚአብሔር ምርጫን ሰጥቶሃል፡፡ እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንድትመጣ ይጋብዝሃል፡፡ ይጠራሃል፡፡
እግዚአብሔር በእምነት ውደ በክርስቶስ ኢየሱስ ወዳለው እምነት እየጠራህ እንዳለ ከተሰማህ (ዮሐ 6፡44) ወደ አዳኝህ ና፡፡ እግዚአብሔር ክፉውን በማንሳት መነፈሳዊ ዕውርነት ካስወገደልህ ወደ አዳኝህ ተመልከት (2ቆሮ 4፡4)፡፡ የህይወትን ነጸብራቅ በሞት ፈንታ እየተመለከትክ ከሆነ በአዳኙ ወዳለው ህይወት ና (ኤፌ 2፡1)፡፡
ስትሞት የት ነው የምትሄደው? መንግስተ ሰማይ ወይንስ ሲኦል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ሲኦል ተወግዶአል፡፡ ኢየሱስን የግል አዳኝህ አደርገህ ተቀበል የእግዚአብሔር መንግስትም የመጨረሻው መድረሻህ ይሆናል፡፡
ሌላ ውሳኔ ብትወስን ሲኦል ደግሞ መጨረሻህ ይሆናል (ዮሐ 14፡6፤ ሥራ 4፡12)
ስትሞት ልትሄድ የምትችልበትን ሁለት ስፍራዎች የተረዳህ ከሆነ እና ኢየሱስ ክርስቶስ የግል አዳኝህ እንደሆነ ካመንክ የሚከተሉትን እንደተረዳህ እርግጠኛ ሁን እና አንደ እምነት እርምጃ በእነዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት አድርግ፡- ‹‹ እግዚአብሔር ሆን እኔ ኃጢያተኛ እንደሆንኩ አምናለሁ አውቃለሁ በኃጢያቴ ምክንያት ለዘለአለም ከአንተ መለየት ይገባኛል፡፡ ሆኖም ግን ባይገባኝም ስለወደድከኝ አመሰግንሃለሁ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የኃጢያቴን መስወዕት ስላዘጋጀህልኝ አመሰግንሃሉ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኔ ኃጢያት እንደሞተ አምናለሁ እናም ለመዳን በእርሱ ብቻ አምናለሁ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ጀምሮ ከኃጢያት ይልቅ ያንተን ህይወት እኖራለሁ፡፡ ቀሪውን ህይወቴን አንተ ላዘጋጀህልኝ አስደናቂ ድኅነት አንድሰጥ እርዳኝ፡፡ ኢየሱስ ሆይ ስላዳንከኝ አመሰግንሃሉ!
English
ስትሞት ወዴት ነው የምትሄደው?