settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ሰይጣን ማን ነው?

መልስ፤


ሰይጣንን በተመለከተ የሰዎች እምነት ከጨቅላ አስተሳሰብ አንሥቶ እስከ ረቂቅ ይደርሳል— ቀንድ ካበቀለ ከትንሽ ቀይ ሰውዬ፣ እሱም ትከሻችሁ ላይ ተቀምጦ ኃጢአት እንድትሠሩ ከሚገፋፋችሁ፣ እስከ የክፋት ስብዕናውን የሚያሳይ ማብራሪያ ድረስ። ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣን ማን እንደሆነና እንዴት ሕይወታችንን እንደሚጎዳ ግልጽ ስዕሉን ይሰጠናል። በቀላሉ ለማስቀመጥ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣን ሲገልጸው፣ እንደ መልአካዊ ሕላዌ እሱም በሰማይ ካለ ሥልጣኑ በኃጢአት ምክንያት የወደቀ፣ አሁንም ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን የሚቃወም፣ ሁሉንም በገዛ ኃይሉ የሚያደርግ፣ የእግዚአብሔርን ዓላማ ለማከላከል።

ሰይጣን የተፈጠረው እንደ ቅዱስ መልአክ ነው። ኢሳይያስ 14፡12 የሰይጣንን ቅድመ-ውድቀት ስም፣ ሉሲፈር በሚል ይሰጣል። ሕዝቅኤል 28፡12-14 ሰይጣን ኪሩቤል በሚል መፈጠሩን ይገልጻል፣ ከፍተኛው የተፈጠረ መልአክ። እሱም በውበቱና በአቋሙ ተኩራራ፣ እናም በከፍታ ላይ ባለው በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ለመቀመጥ ፈለገ (ኢሳይያስ 14:13-14፤ ሕዝቅኤል 28:15፤ 1 ጢሞቴዎስ 3:6)። የሰይጣን ኩራት ወደ ውድቀቱ አመራ። ኢሳይያስ 14:12-15 ላይ ያለውን በርካታ “እኔም” የሚሉ መግለጫዎች ልብ በሉ። በኃጢአቱ ምክንያት፣ እግዚአብሔር ሰይጣንን ከመንግሥተ ሰማያት አገደው።

ሰይጣን የዚህ ዓለም ገዥ ሆነ እንዲሁም በሰማይ ላይ ያለው ሥልጣን አለቃ (ዮሐንስ 12፡31፤ 2 ቆሮንቶስ 4፡4፤ ኤፌሶን 2፡2)። እሱም ከሳሽ ነው (ራዕይ 12፡10)፣ ፈታኝ (ማቴዎስ 4፡3፤ 1 ተሰሎንቄ 3፡5)፣ እና አሳች (ዘፍጥረት 3፤ 2 ቆሮንቶስ 4፡4፤ ራዕይ 20፡3)። ዋነኛ ስሙ “ተቃዋሚ” ወይም “የሚቃወም” ማለት ነው። ሌለኛው መጠሪያው፣ ዲያብሎስ፣ “ሐሰተኛ” ማለት ነው።

ምንም እንኳ እሱ ከሰማይ ቢጣልም፣ አሁንም ዙፋኑን ከእግዚአብሔር በላይ ማድረግ ይሻል። እሱ እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ይቃወማል፣ የዓለምን ስግደት አገኛለሁ በሚል ተስፋ፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ተቃውሞን ያበረታታል። ሰይጣን የእያንዳንዱ የስህተት ያምልኮ ሥርዓትና የዓለም ሃይማኖት ዋነኛ ምንጭ ነው። ሰይጣን ማናቸውንም ነገርና ሁሉንም ነገር በገዛ ሥልጣኑ ያደርጋል፣ እግዚአብሔርንና እግዚአብሔርን የሚከተሉትን ለመቃወም። ሆኖም፣ የሰይጣን መዳረሻ ታትሟል— በእሳት ባሕር ውስጥ ለዘላለም (ራዕይ 20፡10)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ሰይጣን ማን ነው?
© Copyright Got Questions Ministries