ጥያቄ፤
ሊድን ይችላል? ሁሉም ሰው ሊድን ይችላል?
መልስ፤
በዮሐ3፡16፡- ‹‹ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።›› ኢየሱስ በግልጽ በእርሱ የሚያምን ሁሉ እንደሚድን ተናግሮአል፡፡ ‹‹ሁሉ›› የሚለው አንተንና በአለም ያለ ማንኛውንም ሰው ሁሉ ይመለከታል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ደኅነት በእኛ ስራ በሆን ኖሮ ማንም ሰው አይድንም ነበር፡፡ ሮሜ 3፡23፡- ‹‹ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤›› መዝ 143፡2 በተጨማሪ ‹‹ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና ከባሪያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ።›› ሮሜ 10፡3 ያረጋግጥልናል፡- ‹‹ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ››
ራሳችንን ማዳን አንችልም፡፡ ይልቁንም በኢየሱስ ክርስቶስ ስናምን ድነናል፡፡ ኤፌ 2፡8-9፡- ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።›› በእግዚአብሔር ጸጋ ድነናል የጸጋም ትርጓሜ በነጻ የሚሰጥ ነው፡፡ ደህንነት ስለሚገባን አይደለም እንዲሁ በጸጋ እንቀበለዋለን፡፡
የእግዚአብሔር ጸጋ ኃጢያትን ሁሉ ለመሸፈን ብቃት አለው፡፡ (ሮሜ 5፡20) መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢያተኛ በነበሩ እና በዳኑ ሰዎች ህይወት ምሳሌ የተሞላ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ ቀድሞ በተለያየ የኃጢያት ውድቀት ውስጥ ለነበሩት ጽፎአል፤ በዝሙት ለወደቁ ለጣኦተኞች ለሴሰኞች ለግብረ ሰዶማውያን ለቀማኞች ለስስታሞችና ለሰካራሞች፡፡ ነገር ግን ጳውሎስ ስለ ደህኅንነት ነገራቸው 1ኛ ቆሮ 6፡9-11፡- ‹‹ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።››
ሐዋሪያው ጳውሎስ እራሱ አማኞችን የሚያሳድድ ነበር፤ የእሲጢፋኖስን ሞት አጽድቆ ነበር (ሥራ 8፡11) ክርስቲያኖችን እያሰረ በወይኒ ያኖራቸው ነበር ሥራ 8፡3፡፡ በኋላም እንዲህ ብሎ ጻፈ ‹‹ አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ።ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤››
እግዚአብሔር ያልተጠበቁ የማይገባቸውን ሰዎች አድኖ ለራሱ አላማ ይጠቀምባቸዋል፡፡ በደቂቃዎች ውስጥ በመስቀል የተሰቀለውን ሌባ አዳነው፤ (ሉቃ 23፡42-5-43) የቤተክርስቲያን አሳዳጅ ጳውሎስን፤ ከሃዲውን አሳ አጥማጅ (ጴጥሮስ)፤ የሮማውን ወታደርና ቤተሰቡን (ሥራ 10) ሸሽቶ የጠፋውን ባሪያ (አናሲሞስ በፊልሞና) እና ሌሎች ብዙዎችን፡፡ ከእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ውጪ የሆነ ምንም አይነት ማንነት የለም (ኢሳ 50፡2 ተመልከተ)፡፡ በእምነት ምላሽ ልንሰጥና የእርሱን የዘላለም ህይወት ስጦታ ልንቀበል ይገባናል፡፡
ማን ሊደን ይችላል? አንድ ነገር የተረጋገጠ ነው እንርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ ካመንክ ትችላለህ! ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝህ አድርገህ መቀበልህን እርገጠኛ ካልሆነክ አሁን እንደዚህ ያለውን ጸሎት በመጸለይ ምላሽ መስጠት ትችላለህ፡
‹‹እግዚአብሔር ሆይ ኃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቄአለሁ እንዲሁምኃጢያቴ በራሴ መልካም ስራ ወደ ሰማይ ልገባ እንደማልችል አውቄአለሁ፡፡ አሁን እምነቴን ስለእኔ በሞተው የዘላለምን ህይወትን ሊሰጠኝ በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አድርጌአለሁ፡፡ እባክህን ይቅር በለኝና ላንተ እንድኖር አድርገኝ፡፡ ስለተቀበልከኝና የዘላለምን ህይወት ስለሰጠህኝ አመሰግንሃለሁ፡፡››
English
ሊድን ይችላል? ሁሉም ሰው ሊድን ይችላል?