settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ጸሎት ለምን?

መልስ፤


ለክርስቲያን፣ ጸሎት እንደ ትንፋሽ ነው የሚታየው፣ ለማድረግ ቀላል የሆነ፣ ካለማድረግ ይልቅ። በተለያዩ ምክንያቶች እንጸልያለን። ለአንድ ነገር፣ ጸሎት እግዚአብሔርን ማገልገል ነው (ሉቃስ 2፡36-38) እና እሱን መታዘዝ ነው። የምንጸልየው እግዚአብሔር እንድንጸልይ ስላዘዘን ነው (ፊሊጵስዩስ 4፡6-7)። ጸሎት ለእኛ በክርስቶስና በጥንት ቤተ-ክርስቲያን ምሳሌ ሆኖልናል (ማርቆስ 1:35፤ ሐዋ. 1:14፤ 2:42፤ 3:1፤ 4:23-31፤ 6:4፤ 13:1-3)። ኢየሱስ መጸለይ ተገቢ እንደሆነ ካሰበ፣ እኛም ደግሞ ይገባናል። እሱ በአብ ፍቃድ እንዲቆይ መጸለይ ካስፈለገው፣ እኛስ እንዴት መጸለይ ያስፈልገናል?

ለመጸለይ ሌለኛው ምክንያት እግዚአብሔር ጸሎት እንዲደረግ የፈለገበት በብዙ ሁኔታዎች የእርሱን መፍትሔ ለማግኘት ነው። ለዋና ዋና ውሳኔዎች ለመዘጋጀት እንጸልያለን (ሉቃስ 6፡12-13)፤ ሰይጣናዊ መሰናክሎችን ለማሸነፍ (ማቴዎስ 17፡14-21)፤ ለመንፈሳዊው አዝመራ ሠራተኞችን ለመሰብሰብ (ሉቃስ 10፡2)፣ ፈተናን ለማለፍ ኃይልን ለማግኘት (ማቴዎስ 26፡41)፤ ሌሎችን በመንፈሳዊነት ለማጠንከር ብልሃት ለማግኘት (ኤፌሶን 6፡18-19)።

ወደ እግዚአብሔር የምንመጣው ከተወሰኑ ጥያቄዎቻችን ጋር ነው፣ እናም ከእግዚአብሔር ተስፋ አለን፣ ጸሎታችን ለከንቱ እንዳልሆነ፣ የጠየቅነውን በተለየ መልኩ ባንቀበልም (ማቴዎስ 6፡6፤ ሮሜ 8፡26-27)። እሱ ተስፋ ሰጥቶናል፣ ለአንዳንድ ነገሮች እንደ ፈቃዱ ብንለምን፣ የለመንነውን ይሰጠናል (1 ዮሐንስ 5:14-15)። አንዳንድ ጊዜ መልሱን ያዘገየዋል፣ እንደ ጥበቡና ለእኛ ጥቅም። በእነዚህ ሁኔታዎች፣ በጸሎት መጽናትና መቀጠል ይኖርብናል (ማቴዎስ 7:7፤ ሉቃስ 18:1-8)። ጸሎት፣ እግዚአብሔር በምድር ላይ የእኛን ፍቃድ እንዲያደርግ እንደ መሣርያ ተደርጎ መታየት አይኖርበትም፣ ነገር ግን ይልቁኑ እግዚአብሔር ፍቃዱን በምድር ላይ እንዲፈጽም ማድረጊያ እንጂ። የእግዚአብሔር ጥበብ ከእኛ እጅግ ይበልጣል።

የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለይተን በማናውቅባቸው ሁኔታዎች፣ ጸሎት የእርሱን ፍቃድ የማወቂያ መንገድ ነው። ሶሪያዊቷ ሴት፣ ልጇ በጋኔን የተያዘችባት፣ ለክርስቶስ ባትጸልይ፣ ልጇ ባልዳነችላትም ነበር (ማርቆስ 7፡26-30)። ዓይነ-ስውሩ ከኢያሪኮ ውጭ የነበረው ክርስቶስን ባይጠራ ኖሮ፣ ዕውር ሆኖ በቀረ ነበር (ሉቃስ 18፡35-43)። እግዚአብሔር ብሏል፣ ሳናገኝ የምንቀረው ስለማንጠይቅ ነው (ያዕቆብ 4፡2)። በአንድ መልኩ፣ ጸሎት ከሰዎች ጋር ወንጌልን መካፈል ነው። ማን ለወንጌል መልእክት ምላሽ እንደሚሰጥ አናውቅም እስካልተካፈልነው ድረስ። በተመሳሳይ መንገድ፣ መልስ ያገኘ ጸሎትን ፈጽሞ ማየት አንችልም፣ እስካልጸለይን ድረስ።

የጸሎት ማነስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የሚኖረንን እምነትና መታመን ያሳንስብናል። የምንጸልየው በእግዚአብሔር ላይ ያለ እምነታችንን ለመግለጽ ነው፣ ማለትም በቃሉ ቃል እንደገባልን እንደሚያደርግልን፣ ሕይወታችንንም አትረፍርፎ እንዲባርክ፣ ከለመንነው ወይም ተስፋ ካደረግነው በበለጠ (ኤፌሶን 3፡20)። ጸሎት ቀዳሚ መንገዳችን ነው፣ እግዚአብሔር በሌሎች ሰዎች ሲሠራ ለማየት። ምክንያቱም፣ እሱ ከእግዚአብሔር ኃይል ጋር “የምንያያዝበት” መንገድ በመሆኑ፣ እሱም ሰይጣንንና ሠራዊቱን የምናሸንፍበት መንገድ ነው፣ በገዛ ራሳችን ለማሸነፍ አቅመ-ቢሶች በመሆናችን። ስለዚህ፣ እግዚአብሔር በዙፋኑ ፊት ዘወትር የሚያገኘን እንሁን፣ በሰማይ ሊቀ ካህን አለንና እሱም የምንሄድባቸውን ሁሉ ለይቶ የሚያውቅ (ዕብራውያን 4፡15-16)። የእርሱ ተስፋ አለን፣ ማለትም ልባዊ የሆነ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት አለው (ያዕቆብ 5፡16-18)። እግዚአብሔር ስሙን በሕይወታችን ያክብር፣ በእርሱ እንደምናምን ዘወትር በተገባ በጸሎት ወደ እርሱ በመቅረብ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ጸሎት ለምን?
© Copyright Got Questions Ministries